Tuesday, October 15, 2013

በጸለምቲ ወረዳ የሚገኙ መማህራን በማይጸብሪ ከተማ በወረዳ ደረጃ በተደረገው ስብሰባ ተደራራቢ መዋጮ እንዲከፍሉ የቀረበላቸን መመሪያን ተቃወሙ፣




በስርዓት ካድሬዎች መሪነት መስከረም 19,2006 ዓ/ም የተካሄደው ስብሰባ አስተማሪዎቹ የተለያዩ መዋጮዎቹን እንዲከፍሉ ማለት ለአባይ ግድብ ፤ የአባልነት ፤ለመለስ ፋውንዴሽን ፤ ለትግራይ ልማት ፤ የመምህራን ማህበር ወዘተ መዋጨዎችን እንዲከፍሉ ቢጠይቁም መዋጮውን ለመክፈል ፈቃደኛ እንዳልሆነ ገልጸዋል፣
አስተማሪዎቹ ስብሰባውን ሲመሩ ለነበሩ ካድሬዎች የተለያዩ መዋጮዎችን እንድንከፍል የምንገደድ ከሆነ ምን ይቀረናል ብላችሁ ታስባላችሁ ብለው በሚጠዩቁበት ጊዜ ካድሬው ይህ ጉዳይ በኛ የሚፈታ አይደለም አስከፍሉ ተብለን ነው የተላክነው መክፈል አለባችሁ የሚል ምላሽ በመስጠት እንቅጩን ስለነገርዋቸው በርካታ አስተማሪዎች ከአሁን ብሁዋላ ከአባልነት እራሳችንን አግልለናል በማለት መድረኩን ረግጠው መውጣታቸውን ቷውቋል፣
መዋጨውን በመቃወም ስብሰባውን ረግጠው ከወጡት መማህራን መካከል መምህር ሰመረ ገ/መድህን በዲማ አስተማሪ ፤ መምህር አፍወርቂ አስመላሽና መምህር ትዕግስቲ መኮነን የተባሉ አስተማሪዎች ይገኙባቸዋል፣