Thursday, December 26, 2013

በክራይ ቤቶች ስር የሚገኙ መኖርያ ቤቶች። በስርአቱ ባለ ስልጣናትና መንግስት ሰራተኞች ቅድሚያ እየተያዙ መሆናቸው የተገኘው መረጃ ኣስታወቀ፣




በመረጃው መሰረት መኖርያ ቤት ለመስራት ለተቸገሩ ወገኖች በትንሽ ዋጋ ተከራይተው እንዲኖሩበት እየተባለ የህዝብና የመንግስት በጀት ወጥቶላቸው የተገነቡ ቤቶች። በቀዳሚነት ለነዚህ ድሃ ወገኖችና በቤት ክራይ እየተሰቃዩ ላሉ ዜጎች መሰጠት ቢኖርበትም። ከተቀመጠው አላማና አሰራር ውጭ። በቀዳሚነት ለስራአቱ ባለስልጣናትና ለመንግስት ሰራተኞች እየተሰጠ መሆኑ መረጃው አስገንዝበዋል፣
     መረጃው አክሎ እንዳስረዳው። እነዚህ በኪራይ ቤቶች ስር የሚገኙ የስርአቱ ባለስልጣናት፤ ካድሬዎችና የመንግስት ሰራተኞች። በግል ያስገነብዋቸው የግል ቤቶቻቸው በውድ ዋጋ በማከራየት ለራሳቸው ደግሞ የመንግስት ቤት በርካሽ ዋጋ ተከራይተው እየኖሩበት እንደሆነ። ለሚመለከታቸው አካላት ተነገራዋቸው የሚያቁት ጉዳይ ቢሆንም። እስካሁን የወሰዱት አንዳች እርምጃ እንደሌለ የደረሰን መረጃ ገልፀዋል፣