የህወሓት ኢህአዴግ ባለስልጣናት በመቀሌ ከተማ ውስጥ ኣዲ ሃቂና ሃወልቲ በተባሉ የአካባቢው መስተዳደሮች
የሚገኝ ለህዝብ የታደለ ሰፊ መሬት። ከባለ ሃብቶች ጋር በመመሳጠር በሚልዮኖች በሚገመት ብር እየሸጡላቸውና የቀረውም ለራሳቸው ቪላዎች
እየሰሩበት መሆኑን ከቦታው የደረሰን መረጃ ኣስታወቀ፣
መረጃው ጨምሮ እንዳመለከተው የመቀሌ
ከተማ ህዝብ ለመኖርያ ቤት መስርያ የሚሆን መሬት እንዲሰጣቸው ከረጅም አመታት በፊት ያስገቡት ማመልከቻ አወንታዊ መልስ እንዳላገኙበትና።
ይህ አሰራር የስርኣቱ ባለስልጣናት ለግል ጥቅማቸው ካልሆነ። የህዝቡን ጉዳይ የማያገባቸው እንደሆነ የሚያመለክት ነው ሲሉ ምሬታቸው
ገልፀዋል፣
ይህ ኣይነቱ ግለኝነትና ስግብግብነት
የተጠናወተው አሰራር በመቀሌ ከተማ ብቻ የሚታይ ሳይሆን። በአማራ ክልል ደብረማርቆስ ከተማና ሌሎች የአገራችን ከተሞች በሰፊው የእተሰራበት
ያለ እና። ሃላፊነት የጎደለው ኣሰራር መሆኑን ይታወቃል፣