በታህታይ አድያቦ ወረዳ አዲ አሰርና አዲ ፀፀር ውስጥ የሚገኙ አርሶ አደሮች። ደክመው ጥረው ያገኙት የሰብል
ምርት። በወረዳው የሚገኙ የገዥው ስርዓት ፖሊሶች ያለ ህጋዊ መንገድ የእርሻ መሬት ተጠቀማቹህ በሚል ምክንያት። ታህሳስ
10/2006 አ/ም 30 ኩንታል ሰሊጥ ነጥቀው ወደ ጨረታ አውርደው በመሸጥ። ለግል ጥቅማቸው እናዳዋሉትና በተመሳሳይ መንገድ በአዲ
ጎሹና አካባቢው የሚገኙ ታጣቂ ሚልሻና ፖሊሶች በመተባብር የአርሶ-አደሮች ምርት በመንጠቅ ለግል ጥቅማቸው እንዳዋሉት የደረሰን መረጃ
አስታወቀ፣
ከዚህ በተማሳሳይ በሸራሮ ከተማ ውስጥ
የሚኖሩ ከእጅ ወደኣፍ በሆነና በሸቀጣ ሸቀጥ ስራ ላይ የሚተዳደሩ ሴት ወገኖቻችን። ይዘውት ለነበሩ ሸቀጣ ሸቀቶች በፖሊሶች በመነጠቁ።
በከባድ ችግር ላይ በመውደቃቸው። ወደ ሚመለከታቸው አካሎች ቀርበው ላሰሙት አቤቱታ ሰሚ ጀሮ እንዳላገኙለትና እስካሁንም ብሶታቸው
በመግለፅ ላይ መሆናቸው ታውቀዋል፣
ይህ በእንዲህ እንዳለ በሸራሮ ከተማ
ለእለታዊ ኑሮ የሚያገለግል የምግብ ሸቀጣ ሸቀጥ አቅርቦት ጠቅልሎ በመጥፋቱ ምክንያት። ለእያንዳንዱ ነዋሪ በወር ግማሽ ሊትር የምግብ
ዘይት፤ እንድ ኪሎ ሱኳር ከቀበሌ ገዝቶ እየተጠቀመ መሆኑና። በአጋጠመው የንፁህ መጠጥ ውሃ እጥረትም ለተለያዩ ውሃ ወለድ በሽታዎች
እንደተጋለጠ መረጃው አክሎ አስረድተዋል፣