Thursday, December 26, 2013

በሁመራ ከተማ ውስጥ የኤሌክትሪክ ሃይልና ኔት-ዎርክ በተደጋጋሚ በመቆራረጡ ምክንያት። በነዋሪዎቹ ላይ ማህበራዊና ኤኮኖሚያዊ ችግር እያጋጠመ መሆኑን ከከተማዋ የተገኘ መረጃ ኣስታወቀ፣




በምእራብ ትግራይ ዞን ሁመራ ከተማ ውስጥ የኤሌክትሪክ መብራት ከጠፋ ረጅም ግዜ አስቆጥሮ ባለበት ግዜ። ኔት-ወዎርክም ከተቋረጠ ከአንድ ወር በላይ በማስቆጠሩ ምክንያት። የአካባቢው ህብረተሰብ እለታዊ ኑሮውን ለመምራት ተቸግሮ እንዳለና። በተለይ ባለ ድርጅቶችና ነጋዴዎች ይህን  የኔት-ዎርክና  የኤሌክትሪክ መብራት መቆራረጥ በኢኮኖሚያቸው ላይ ትልቅ ኪሳራ እያደረሰ መሆኑን ታውቋል፣
    በከተማዋ የሚገኙ ለህዝብ አገልግሎት የሚሰጡ እንደ ሆስፒታል፤ ባንክ ቤትና የመሳሰሉት ድርጅቶች። በኤሌክትሪክ ሃይል እጦት ምክንያት ተገቢ አገልግሎት ለመስጠት ባለመቻላቸው። የአካባቢው ህዝብ በመስተዳደሩ ላይ ጥያቄ ባነሳበት ባሁኑ ወቅት። ከሁመራ አስተዳደር ባለሃብቶች ስለተከራዩት ነው የሚል መልስ እንደተሰጠና። ይህንን የህዝብ ችግር ተከታትሎ የሚፈታ የመንግስት አካል ባለመኖሩ ነዋሪዎቹ ምሬታቸው በመሰማት ላይ መሆናቸው ከከተማዋ የደርተሰን መረጃ ያስረዳል፣
    ይህ በእንዲህ እንዳለ በሁመራ ውስጥ ንፁህ የሚጠጣ ውሃ ካቛረጠ ከሁለት ሳምንት በላይ በማስቆጠሩ። ችግር ላይ የወደቁ የከተማዋ ነዋሪዎች። ጥራቱ ካልጠበቀ ከተከዜ ወራጅ ወንዝ ቀድተው ለመጠቀም ግድ ስለ ሆነባቸው። እለታዊ ኑሮኣቸው ለመምራትና ጤንነታቸው ለመጠበቅ እንዳልቻሉ። በጤና ሞያ ከተሰማሩ የአካባቢ ነዋሪዎች ከተገኘ መረጃ ለማወቅ ተችለዋል፣