በደቡብ ትግራይ ዞን
የሚገኘው የማይጨው ከተማ ነዋሪ ህዝብ። የተለያዩ ማህበራዊ አቅርበቶች በማጣቱ ምክንያት ችግር ላይ በመውደቁና። በተለይ ባሁኑ ግዜ
ከከተማዋ ስኳር ጠቅልሎ መጥፋት ከጀመረ በርከት ያለ ቀናት በማስቆጠሩ። በከተማው ውስጥ የሚገኙ ሬስቶራንት፤ ቁርስ ቤቶች ካፌዎችና
ሌሎች ከሱ ጋር ተያያዥነት ያለቸው ድርጅቶች ከፍተው ሲሰሩ የቆዩ ባለሃብቶች። ለትልቅ ኪሳራ በመጋለጣቸው። ንግድ ፈቃዳቸውን እንዲሰርዘላቸውና
ድርጅታቸውን እንዲዘጉ ማመልከቻ እያስገቡ መሆናቸው የደረሰን መረጃ ኣስታወቀ፣
ከከተማው ስኳር የመጥፋቱ ሁኔታ ቀናቶች አስቆጥሮ ባለበት ባሁኑ ግዜ።
የዞኑ ባለስልጣናት በህዝቡ ላይ አጋጥሞ ያለውን ችግር ግምት ውስጥ በማስገባት መፍትሄ ማምጣት ስላልቻሉና። ባለ ንግድ ድርጅቶቹም
በጥቁር ገበያ እየገዙ ስራቸውን መቀጠል ስላልቻሉ። አጋጥሞ ላለው
የስኳር እጥረት ግምት ውስጥ ያላስገቡ የአከባቢው አስተዳዳሪዎች። በንግድ ፈቃድ ስም ስኳሩን ይዘውታል በማለት። በላያቸው ላይ ፍትሃዊ
ያልሆነ ግብር ለማስከፈል ላይና ታች እያሉ እንደሚገኙና በዚህም ምክንያት ባለሃብቶቹ ድርጅታቸውን እየዘጉ መሆናቸው ለማወቅ ተችለዋል፣