በአሁኑ ጊዜ በአ/አበባ ከተማ እየታየ ባለው ከፍተኛ የኑሮ ውድነት ህይወታቸውን መምራት የተሳናቸው በከተማዋ
የመብራት ሃይል ተመድበው ለአመታት ሲያገለግሉ የቆዩ የመንግት ሰራተኞች መንግስት ችግራችንን ተረድቶ ለምን የደምዎዝ ጭማሪ አያደርግልንም?
የደምዎዝ ጫማሪ ጥያቄ የሁሉም የመንግስት ሰራተኞች መሰረታዊ ጥያቄ መሆኑን ተገንዝቦ መንግስት ጭማሪ ማድረግ ይገባዋል በማለት በስብሰባ
በመጠየቃቸው ብቻ ከስራቸው መባረራቸውን ለማወቅ ተችሏል።
አባዛኛው ሰራተኛ በቂ ድምዎዝ ስለማይከፈለው ኑረውን ለመምራት በተቸገረበት በአሁኑ ጊዜ አመራሩ ቦታ ላይ
ያሉ ግለሰቦች ስልጣንን አለአግባብ በመጠቀም ከሚያገኙት ገቢ ጋር የማይመጣጠን በኖሪያ ቤቶች ሲታሰሩና በውጭ ሃገር ገንዘብ ስታስቀምጡ
ይታያል በማለት በስብሰባ በይፋ በመናገራቸው ቅር የተሰኙ የመስሪያ ቤቱ ባለስልጣናት ከ 200 የሚበልጡ ስራተኞችን እንዲባረሩ አድረገዋል።
መንግስት
ጥያቄ በማቅረባቸው ብቻ ከስራ የተባረሩትን ሰራተኞችን በመብራት ሃይል ውስጥ የተለያዩ ደባዎችን በመፈፀም መብራት እንዲቋረጥና ህዝቡ
አገልግሎትን በአግባቡ እንዳያገኝ ሲያደርጉ የቆዩ ጸረ-ህዝብ ናቸው በማለት ለፖለቲካ ፍጆታ እያዋለው መሆኑን የደረሰን ዘገባ ያመለክታል።