Tuesday, January 14, 2014

በመቀሌ ከተማ በቴክኒክ ሞያና በኮብልስቶን ስራ የሰለጠኑ ወጣቶች በጨረታ ኣሰጣጥ ላይ ተደጋጋሚ ችግር እንዳለና መፍትሄ እንዳልተገኘለት የተገኘው መረጃ ኣስታወቀ፣




በመቀሌ ከተማ የሚገኙ ወጣቶች ወደ ስራ ትሰማራላቹህ ተብለው በቴክኒክ ሞያና በኮብልስቶን ስራ ከሰለጠኑ በኅላ፤ በታህሳስ 26/2006 ኣ/ም ለሁለተኛ ግዜ ጨረታ በተመለከተ ስልጠና እንዲወስዱ ጥሪ ቢደረግላቸውም፤ ኣስቀድመን የወሰድነው ስልጠና ሳንጠቀምበት ሌላ ስልጠና መውሰዱ ያልተፈለገ ግዜ ማጥፋት ካልሆነ በስተቀር ሌላ ፋይዳ ሊኖረው ኣይችልም በማለት ላቀረቡት ጥያቄ ኣወንታዊ ምላሽ እንዳላገኙለት ተገልጸዋል፣
   እነዚህ ብስራ ኣጥነት ምክንያት የቤተሰባቸው ሸክም ሆነው የቆዩ ወጣቶች ስልጠናቸው ካገባደዱ ብኃላ በከተማው ውስጥ ይሰራል ተብሎ በጀት ለወጣለት የድንጋይ ንጣፍ መንገድ በኮንትራት ሊሰጣቸው በጠየቁበት ግዜ በቂ ባልሆነ ምክንያት እንዳይሰሩ እንደተደረገና፤ ይሀው የድንጋይ ንጣፍ መንገድ መሰራት ያለበት ግዜው ኣሁን መሆኑ እየታወቀ ለተፈጠረው የስራ እድል ለኛ ላለመስጠት ብለው ምክንያታዊ ባልሆነ መንገድ ወደ ክረምት ወር እንዲሸጋገር መደረጉም ተገቢ እንዳልሆነና ላልተፈለገ የጉልበትና  የፋይናንስ ችግር የሚያጋልጥ እሰራር ነው ሲሉ እንደተናገሩ    ለማወቅ ተችለዋል፣
 ይህ በንዲህ እንዳለ መንግስት መሃስንዲሶች በተመለከተ ከሚናገር ኮንትራቱ ከተሰጠንና ግነዘቡን ከተከፈለን በሃላ እኛው ራሳችን ለምን መሃንዲስ ቀጥረን ኣናሰራም፤ መንግስት እየተከተለው ያለው የስራ ሂደት ለኣሰሪውና ለስራው ዋስትና የሚሰጥ ኣይደለም ብለው ላቀረቡት ጥያቄ ተገቢ የሆነ መልስ እንዳላገኙለት ለማወቅ ተችለዋል፣
 ባሁኑ ግዜ በዲግሪና በዲፕሎማ ተመርቀው የቤተሰባቸው ሸክም ሆነው የሚገኙ ወጣቶች ብዙዎች ቢሆንም፤ በስልጣን ላይ ያለው መንግስት ግን ለነዚህ ስራ ኣጥ የተማሩ ወጣቶች በቅድምያ የኮብልስቶን ስራው ይሰጣቸዋል ብሎ ተናግሮ ሲያበቃ በተግባር ግን ቅድምያ በጥቅም ለተሳሰሩትና ለዘመዶቻቸው እንደሚሰጥዋቸው የተገኘው መረጃ ኣክሎ ኣስረድተዋል፣