Tuesday, January 14, 2014

በመቀሌ ከተማ በኮንደምንየም ስም የተገነቡ በርከት ያሉ የህዝብ መኖርያ ቤቶች ባሰራራቸው ላይ ጥራት የጎደላቸው መሆኑንና ተጠቃሚዎቹ ለከባድ ችግር ተጋልጠው እንደሆኑ የተገኘው መረጃ ኣስታወቀ፣




እነዚህ በመቀሌ ከተማ በኮነደሚንየም መኖርያ ቤቶች ሰፍረው የሚገኙ ህብረተሰብ የሚኖርበት ቤት ከመጀመርያውኑ ባሰራሩ ላይ ጥራቱ ያልጠበቀና በጥንቃቄ ያለተገነባ ከመሆኑ የተነሳ ለችግር መጋለጣቸው የገለፀው መረጃው፤ በተለይ የሽንት ቤቱ ፍሳሽ ከመተላለፍያው ትቦ እየፈነዳ ወደ መኖርያ ቤቱ ውስጥ በመግባቱ ምክንያት፤ ነዋሪው ህብረተሰብ በመጥፎው ሽታ ምክንያት ለተለያዩ በሽታዎች መጋለጣቸው ሊታወቅ ተችለዋል፣
    በዚሁ መጥፎ ሽታና የሽንት ቤት ፍሳሽ ተበክለው ያሉ ኣካባቢዎች ኣዲ ሃቂ፤ ሓወልትና እንዳ ገብርኤል እየተባሉ የሚጠሩ መንደሮች ሲሆኑ፤ እስካሁን ድረስም የሚመለከታቸው ኣካላት ኣንዳችም መፍትሄ እንዳላደረጉለት መረጃው ኣክሎ ኣስረድተዋል፣
    ባሁኑ ግዜ በተለያዩ ያገራችን ኣካባቢዎች በመንግስት እየተገነቡ ያሉ የኮንደምንየም መኖርያ ቤቶች ብቃትና ጥራት የሌላቸው ከመሆኑ የተነሳ ነዋሪው ህዝብ ለትልቅ ችግር ተጋልጦ ለሚያቀርበው ተደጋጋሚ ጥያቄ ሰሚ ጀሮ እንዳላገኘለትና በተለያዩ ኣጋጣሚዎች ብሶቱን መግለፁ ይታወቃል፣