Thursday, March 19, 2015

በደቡብ ጎንደር ዞን ምስራቅ እስቴ ወረዳ የሚኖር ህዝብ መንግስት ትኩረት ሰጥቶ ድጋፍ ሊሰጠን አልቻለም ሲሉ ምሬታቸውን መግለፃቸው ምንጮቻችን ከቦታው አስታወቁ፣



   እንደምንጮቻችን ገለፃ። በደቡብ ጎንደር ዞን ምስራቅ እስቴ ወረዳ ዙሪያና የመካነ-እየሱስ ከተማ ህዝብ መጪውን ምርጫ አስመልክቶ በተደረገላቸው ተደጋጋሚ ስብሰባ ላይ መንግስት ሊያግዘን የሚገባውን እገዝና ድጋፍ ሊያደርግልን ካለመቻሉ ባሻገር። በተለያዩ ጊዜያት የሚነሳውን ችግር ከነፋስ መውጫ መካነ እየሱስና እንዲሁም ደብረታቦር የሚያገናኘውን የተበላሸ መንገድ አስፋልት እናደርጋለን በሚል ከህዝብ የተሰበሰበ ገንዘብ የመንግስት ተወካዮች ለግል ጥቅማቸው ማዋላቸው። በመጭው ምርጫ ላይ ምን ልንመርጥ እንደምንችል ትልቅ ማሳያ ነው ሲሉ መናገራቸውን አስረድተዋል፣
   ይህ በእንዲህ እንዳለ ከመካነ እየሱስ ጋሳይ ጋይንትና ወደ ደብረ ታቦር የሚያገናኝ መንገድና የመካነ እየሱስ ከተማ የውስጥ ለውስጥ መንገድና የውሃ ማፋሰሻ ቱቦ ይሰራል እየተባለ ያልተሰራበትን   ምክንያት። የከተማውን ከንቲባ  ወንድምነው ክንዱ ሲናገር ከዞን የበጀት እጥረት ስላገጠመ ነው ሲል መናገሩ ለማወቅ ተችሏል፣