መረጃው እንደገለፀው በጥር 7 2006 ኣ/ም ለኣባይ ግድብ መስርያ ተብሎ በታርጋ ቁጥር ኮድ 3-66303
ኣ/ኣበባ የሆነች መኪና ተጭኖ ሲሄድ የነበረ ቴንዲኖ፤ ጣውላ፤ ስካፋና ሌሎች የህንፃ መሳርያዎች በኣማራ ክልል ባህርዳር ከተማ ውስጥ
ከደረሰ በኋላ ኣቶ ፍቅሩ ኣሰፋ ለተባለ ተባባሪ ባለ ሃብት ተሽጦ እየተራገፈ እያለ ከሰራተኞች ጋር በተነሳው ግርግርና ያለመስማማት በፖሊስ ሊያዝ እንደተቻለ ተገለፀ፣
መረጃው በማስከተል የተያዘው ንብረት
ለኣባይ ግድብ መስርያ እንዲውል ተብሎ የተላከ እንደነበረ ፖሊሶቹ ካወቁ በኋላ እንዳይታሰርና እንዳይጠየቅ የፈራው የተሽከርካሪዋ
ሾፌር መኪናዋን ጥሎ ከቦታው እንደተሰወረ ተገለፀ፣
በተመሳሳይ መንገድ በኣባይ ግድብ ውስጥ
ስራ ላይ ተሰማርተው የነበሩ 15 የሚሆኑ ጀነሬተሮች የፕሮጀክቱ ሃላፊዎች
ተበላሽተዋል በሚል ምክንያት ከቦታው ኣስወጥተው በመሽጥ ለግል ጥቅማቸው ኣንዳዋሉት፤ የፕሮጀክቱ ምክትል መሃንዲስና ንብረት ክፍል
ሃላፊ የሆነው ኣቶ ታምራት ኣስረስ በጥር 2 /2006 ኣ/ም ኣጋለጠ፣
ኣቶ ታምራት ኣስረስ እየተጠፋፋ ያለው
የሃገርና የህዝብ ንብረት እንዲያጋልጥ የተገደደው ከግዜ በኋላ በወንጀል ሊጠየቅ እንደሚችል ተረድቶ መሆኑን የገለጸው መረጃው ሓላፊዎቹ
በላዩ ላይ ሊፈፅሙት ከሚችሉት ጫና ለመዳን ሲልም ከስራው ራሱ እንደተሰናበተ መረጃው ኣክሎ ኣስረድተዋል፣