ምንጮቻችን የላኩልን
መረጃ እንደሚያመለክተው የናዕዴር ዓዴት ወረዳ አስተዳዳሪ የሆኑ የህወሃት ካድሬዎች የአካባቢው ማህበርሰብ በአስገዳጅ ማዳበርያ እንዲውስድና
ከአቅም በላይ ግብር ሲያስከፍሉት በነበሩት ባለ-ስልጣኖች ላይ ቅሬታ ይዞ እንደሚገኝ ቀድመው የተረዱ ካድሬዎች በመጪው ምርጫ ላይ
አይመርጠንም የሚል ስጋት ስላደረባቸው ለህብረተሰቡ ስብሰበው የማታለያ ቅስቀሳ ያደረጉለት ሲሆን በዚህ ቅስቀሳ ላይም የማዳበርያ
ክፍያ ዋጋ እንቀንስላችኋለን ለቀጣይም ማዳበሪያ ውሰዱ ብለን አናስገድዳችሁም የሚል የማይተገብር ቃል እንደገቡላቸው ለማወቅ ተችሏል።
መረጃው ጨምሮ እንዳስረዳው በወረዳው የሚገኙ ካድሬዎች የነጋዴዎችን ገቢና ወጪ ሳያውቁ በግምት ከአቅም በላይ ግብር እያስከፈሉ ለከፍተኛ የእዳ ሰለባ እያደረጓቸው እንደሚገኙ የገለፀው መረጃው ለገበሬው
ማህበረሰብ ደግሞ ያለፍላጎቱ ማዳበርያ እንዲወስድ በማስገደድ አርሶ የሚያገኘው ምርትና የሚከፍለው ግብር ሲነፃጸር ፍፅሞ ስለማይገናኝ
ለኪሳራ እንድተጋለጡ መረጃው አክሎ አስረድቷል።