Saturday, January 11, 2014

የወያኔ ኢህኣዴግ መከላከያ ሰራዊት የኣገልግሎት ግዜ በመጨረሳቸው ምክንያት ላነሱት የስንብት ጥያቄ ተገቢ መልስ ስላላገኙለት ወደ ሚመቻቸው ቦታ እየጠፉ መሆናቸው ተገለፀ፣



ተግባር ላይ በማይውል ቃል ተታለው በስራኣቱ መከላከያ ሰራዊት ተቀጥረው ከሰባት ኣመት በላይ ሲያገለግሉ የቆዩ በርከት ያሉ የሰራዊት ኣባላት። በህገ ደንቡ መሰረት የሰራዊት ኣገልግሎታቸው ጨርሰው ህጋዊ የስንብት ፍቃድ እንዲሰጣቸው በተደጋጋሚ ጥያቄያቸው ቢያቀርቡም። ሰሚ ኣካል ባለማግኘታቸው ምክንያት። እየጠፉ መሆናቸው ያገኘነው መረጃ ኣስታወቀ፣

     ይህን ኣይነት ጥያቄ በሁሉም ያገራቸን ኣካባቢዎች በሚገኙ የመከላከያ ሰራዊት የሚነሳ ቢሆንም። በተለይ ባሁኑ ግዜ ተጋኖ እየታየ ያለው በምእራብ እዝ በ24ኛ ክፍለጦር የሚገኙ የሰራዊቱ ኣባል እንደሆነና። በኣብዛኛዎቹ የሰራዊቱ ኣባላትም ስርኣት ባለው መንገድ እንደገባነው ሁሉ ኣሁንም በተገቢው መንገድ የስንብት ፍቃድ መሰጠት ኣለብን በማለት ኣቤቱታቸው እያቀረቡ መሆናቸው የገለጸው ይሀው መረጃ። የሰራዊቱ የበላይ ኣዛዦች በተገኙበት መድረክ ጭምር የተቃውሞ መልእክት ያለው ጥያቄ ቢያቀርቡም። ሰሚ ጀሮ ባለማግኘታቸው ምክንያት። ትልቅ ውጥረት ሰፍኖ እንዳለ ሰራዊቱ ውስጥ ካሉ ምንጮች ለመረዳት ተችለዋል፣

     ፀረ ህዝብ በሆኑ የስርኣቱ ባለስልጣኖች ችግር ውስጥ የገቡ የምእራብ እዝ 24ኛ ክፍለጦር መከላከያ ሰራዊት። የስንብት ጥያቄ ኣቅርበው መልስ ባለማግኘታቸው ምክንያት በታህሳስ 25/2006 ኣ/ም ቁጥራቸው የማይናቅ የሰራዊቱ ኣባላት ሓሽማ ወደተባለች የሱዳን ከተማ ሲሄዱ እንደተያዙና። ከነዚህም ፊልሞን ዘበርሀና መሃመድ ዳንኤል የተባሉት ወታደሮች። ማይ ካድራ በተባለው ከተማ ታስረው እንደሚገኙ መረጃው ጨምሮ ኣስረድተዋል፣