የህ.ወ.ሓ.ት ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ አመራሮች
እንደልማዳቸው ለትንሽ ነገር እያጋነኑ ለጥፋት እንደ ልማት ለፍትህ እና ዴሞክራሲ እጦት መልካም አስተዳደር ነገሰ እያሉ።
በዚህ ነጋ ጠባ ለጉጅሌያቸው ሲወድስ የማይሰለቸው እና ራሳቸው በተቆጣጠሩት የህዝብ ንብረት
በሆኑ ሚዲያዎች አድርገው። ጭቁን ህዝባችን ዙርያ መለስ በድህነት አዘቅት ሂወቱ እየመራ ባለበት ሁኔታ እንደተጠቀመ እንዳለ አስመስለው
እያዜሙለት ይገኛሉ፣
እነዚህ በግላዊ ጥቅም የታወሩ ከሃዲያን መሪዎች ለህዝባችን እያደናገሩና ለፀረ
ህዝብ አስተዳደራቸው ተቃዉሞ ለተንቀሳቀሰ ዜጋ እየረገጡ።
በመላው አገራችን ኢ-ዴሞክራስያዊ አስተዳደርና ጠባብነት በማስፈን እነሱ በዘመቱት
የሃገርና የህዝብ ሃብት ሲኩራሩ፣ ድሃ ህዝባችን ግን በከፍተኛ ድህነት እየወረደው ባለ ማለቅያ የሌለው ችግሮች እየተሰቃየ የሚሰማው አካል አጥቶ በችግር ላይ ይገኛል፣
ከመሰረቱ የዚህ ጉጅሌ አመራሮች የማደናገር እንጂ የተግባር ሰዎች አይደሉም፣
ይህ ፀረ ህዝብ አስተዳደራቸው ደግሞ ባለፉት 22 ዓመታት የስልጣናቸው እድሜ ለማራዘም ህዝባችን በረሃብ እና በኋላቀር እያለ የሃገር
እና ህዝብ ሃብት እየመዘበሩ ያ የተለመደው ፀረ ህዝብ ተግባራቸው አጠናክረው እየቀጠሉበት ይገኛሉ፣
ዛሬ በተለያዩ የአገራችን ክልሎች የሚገኙ እስር ቤቶች በታሰሩ ሰዎች ሞልተው
ተጭናንቀዋል፣ የህወሓት ኢህአዴግ ደጋፊዎች አይደላቹም የተቃዋሚ ፓርቲዎች ተባባሪዎች ናቹህ ወዘተ እየተባሉ ወደ እስር ቤት እየታጎሩ የሚገኙ ዜጎቻችን በርከት ላለ ዓመታት እንዲታሰሩ በማድረግ ለስቃይ እና ለሞት እንዲዳረጉ ሲያድርጋቸው
በተለያየ ምክንያት እያሳበቡም የስርዓቱ የፀጥታ አባላት በሰላማዊ ዜጎቻችን
ላይ አነጣጥረው በመተኮስ ሂወታቸው እንዲያጡ እያደረጉ ይገኛሉ፣
በዚህ መሰረት፦
በመተማ ወረዳ ህጋዉነት በሌለው መንገድ ተደራጅተው ወደ ሱዳን እየተሻገሩ
የነበሩ የ10ኛ ክፍል ተማሬዎች ፈደራል ፖሊስ በከፍቱባቸው የቶክስ
ሩምታ አብረሀት ኣወቀና ታምሩ ቸኮለ የተባሉ ዜጎቻችን ሲገደሉ ሌሎች 4 ቆስለዋል፣
በቅርብ ግዜ
ደግሞ የጥርጊያ መንገድ ሰራተኞች በአዲስ ኣበባ ከተማ በብርድ ልብሶች የተጠቀለሉ አስካሬኖች አግኝተዋል፣
የወያኔ-ኢህአዴግ
አመራሮች በሚያድረጓቸው ስብሰባዎች ላይ የመብት ጥያቄ ላነሱ ዜጎቻችን አነሻሾች ተብለው በላያቸው ላይ ብዙ ግፍ ይፈጽሙባቸዋል
ያጠፋዉዋቸዋልም፣
የህወሓት ኢህአደግ ጉጅሌ በጋህድ እና በስዉር በጭቁን ህዝባችን የተለያየ
በደሎች በመፈፀም የስልጣኑ እድሜ ለማራዘም ላይ ታች እያለ የሚገኝ
ስርኣት ነው፣
ስለዚ ሁሉም
የህዝባችን ስቃይ እና መከራ አብቅቶ ለአገራችን የሚጠቅም ስርዓት
ለማስፈን አንድነታችን አጠናክረን ለዚህ እየባሰ እየሄደ ያለው የወያኔ
ኢህአዴግ ስርዓት ከስልጣኑ ለመጣል እንታገል፣