በእለቱ በተካሄደው የበአሉ አከባበር ስነ-ስርአት በርከት ያሉ ጥሪ የተደረገላቸው
እንግዶች፤ የድርጅቱ አባላትና የትግሉ ደጋፊዎች፤ የድርጅቱ ከፍተኛ አመራሮችና ታጋዮች የተገኙ ሲሆኑ በተለይ የትህዴን ታጋዮች ለየካቲት
19 ክብር የሚገልፁ መፈክሮችና ዘፈኖች በማሰማት በአሉ ወደ ተዘጋጀበት ቦታ ከደረሱ በኋላ መድረኩ የሰማእታት የህሊና ፀሎት በማድረግ
እንዲከፈት ተደርገዋል።
በማስከተል የመድረኩ አስተባባሪዎች ለበአሉ ተካፋዮች ሰላምታ ካቀረቡና
በድርጅቱ የባህል ቡድን በአሉን አስመልክተው ዘፈን ካቀረቡ በኋላ የትህዴን ምክትል ሊቀመንበር ጓድ መኮነን ተስፋይ የድርጅቱ መግለጫ
አቀርበዋል።
ጓድ መኮነን ባቀረበው ንግግር ላይ ለበአሉ ተካፋዮች እንኳን ወደዝች
የተቀደሰች እለት አደረሳቹሁ አደረሰን በማለት። የዛሬውን የካቲት 19 በአል ድርጅታችን ከማንም ግዜ በላይ ተጠናክሮ፤ የህዝቡን
አደረጃጀትና ውስጣዊ አሰረር በተቀናጀ መንገድ ፈሩን ይዞ፤ አጠቃላይ በህብረተሰቡ ውስጥ ትልቅ ተቀባይነት ባገኘንበት ሁኔታ ላይ
ሆነን በአሉን እያከበርን ሲል ገልፀዋል።
በዚሁ ትልቅ ክብር የሚሰጠው የድርጅቱ በአል በድምቀት ለማክበር ሰፊ የሆነ
ዝግጅት እንደተደረገና ከዝግጅቱ መሃልም ድል ለጭቁኖችና ማእበል በተባሉ የድርጅቱ የባህል ቡድን የተለያዩ አዳዲስ ዘፈኖች፤ በአማርኛና
በትግርኛ የተዘጋጁ ድራማዎችና ኮሚዲዎች መድረኩ ላይ ቀርበዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በተካሄደው በአል ላይ ትኩረት ከሳቡ ዝግጅቶች አንዱ
የድርጅታችን ልሳን የሆነችው ብስራት መፅሄት ባለፈው ወቅት በትግርኛ ቋንቋ ብቻ ስትታተም እንደቆየች የሚታወቅ ሆኖ አሁን ግን ለሁሉም
የአገራችን ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ማእከል በማድረግ መልእክትዋን ለማስተላለፍና ህብረ ብሄራውነትዋን ለማረጋገጥ በሚመቸው መልክ
ተዘጋጅታ ወደ አንባቢዎችዋ ቀርባለች።
የተከበራቹሁ አድማጮቻችና ተመልካቾቻችን የበአሉን ሙሉ ዝግጅት በተመለከተ
በቀጣይ ፕሮግራማችን እናቀርበዋለን።