በአዊ ዞን አፋት ወረዳ
ደቅ ቀበሌ 01፤ ዘረ-ገነት፤ ቡኒጅራና ወርቅ-ሃገር ከተባሉት አካባቢዎች የተውጣጡና የፀጥታ አስከባሪዎች በሚል የተደራጁ
ታጣቂዎች ከታህሳስ ወር እስከ የካቲት 12/2006 ዓ/ም የተለየ አመለካከት ያላቸውና በተቃዋሚ ድርጅት ጎራ የተሰለፉ ተብለው በስርአቱ
የተፈረጁ ከ325 በላይ ንፁሃን ወገኖቻችን በደረሰባቸው ድብደባ ምክንያት አካል ጉዳተኞች እንደሆኑ የገለፀው መረጃው ሌሎች በርከት
ያሉ ዜጎቻችን ደግሞ ታስረው ሲደበደቡ ከቆዩ በኋላ በየካቲት 12/ 2006 ዓ/ም በአዘጋጁት የተሃድሶ መድረክ ላይ በስህተት ነው
የታሰሩት ይቅርታ አድርጉልን በማለት የአዞ እንባ እያነቡ እንደዋሉ ለማወቅ ተችለዋል።
በወቅቱ ለማስመሰል ተብሎ በታጣቂዎቹ ስህተት አካላቸው ለተጎዱና ለተደበደቡት
ካሳ ለመስጠትና የፀጥታ አስከባሪ በአል ተብሎ በተዘጋጀው የይስሙላ መድረክ ላይ ሲያስተባብሩ የነበሩ የህወሃት ኢህአዴግ ተላላኪዎችና
የምክር ቤት አባል የሆኑት አቶ የኔው አበበ፤ የወረዳው ጽሕፈት ቤት ኢኒስፔክተር አቶ ባደግና ሌሎች የዞኑ ጽሕፈት ቤት ሃላፊዎች
በቦታው ተገኝተው ባሰሙት ንግግር ላይ በፀጥታ አስከባሪዎች ተደብድቦ አካል ጉዳተኛ የሆነ ማንኛውም ሰው ተዘጋጅቶ ካለው መድረክ
ውጭ ፍትህና ፍርድ ማግኘት እንደማይችል ማወቅ አለበት ሲሉ የማስፈራርያ ንግግር በመስጠታቸው ምክንያት ከነበረው ተሳታፊ ውስጥ ከግማሽ
በላይ የሚገመት መድረኩን ረግጦ እንደተበተነ ከተገኘው መረጃ ለማወቅ ተችለዋል።
ይህ በእንዲህ
እንዳለ ብአዊ ዞን አንከሻ ወረዳ የሚገኙ በጸጥታ አስከባሪ ስም የተሰማሩ የስርአቱ ታጣቂዎች በሰላማዊው ህዝብ ላይ አሰቃቂ ግፍ
በመፈፀም ላይ እንዳሉና በየካቲት 2/ 2006 ዓ/ም 4፣00 አካባቢ ላይ ከአዘና ወደ አዩ
ስትሄድ የነበረች የህዝብ ማመላለሻ አውቶብስ ቀበሌ እያስታ
ከደረሰች በኋላ ሁለት የፖሊስና ኣባላትና ሌሎች ስምንት የሚሆኑ የፀጥታ አስከባሪዎች በመሆን አውቶብስዋን እንደዘረፍዋት ምንጮቻችን
ከአካባቢው አክልው አስረድተዋል።