Wednesday, March 5, 2014

የአድዋ ከተማ ነዋሪዎች የትህዴን ፓምፕሌ በእጃቹህ ተገኝተዋል እየተባሉ በታጣቂዎች ተይዘው እየታሰሩ መሆናቸው ተገለፀ።



በትግራይ ማእከላዊ ዞን የአድዋ ከተማ ነዋሪ ለሆነው ህዝብ የትህዴን ፓምፕሌት አነበባቹህ ቅስቀሳ አካሄዳቹህ በሚል ምክንያት በከተማው ውስጥ ማንዴላ በመባል በቅፅል ስሙ ለሚታወቅ እና አቶ ብርሃኔ ፋሎ የተባሉት እንደታሰሩና ሌሎችም እየታሰሩ መሆናቸው ለማወቅ ተችሏል።
    በከተማው ታስረው ያሉ ወገኖቻችን እለታዊ ስራቸው በማከናወን ላይ እያሉ በየካቲት 8/2006 ዓ/ም በስርአቱ ታጣቂዎች ተይዘው እንደታሰሩ የገለፀው መረጃው ለምን እንደታሰሩ እንዲነገራቸው በጠየቁበት ሰዓትም የትህዴን ፓንፕሌት በእጃቹህ ተገኝተዋል በሚል ምክንያት እንደሆነ የገኘነው መረጃ አስረድተዋል።
     በአሁኑ ግዜ የወያኔ ኢህአዴግ ስርአት የኔ ወገን ነው እያለ በሚያሞካሽበት ህዝብ ላይ እያወረደው ያለ በደልና ግፍ ለህዝቡ ምንም ዓይነት ተቆርቋሪነት እንደሌለው የሚያሳይ ግልፅ የስርአቱ ባህሪ ነው ሲሉ አንዳንድ የከተማዋ ነዋሪዎች መግለፃቸው ታውቀዋል።