Wednesday, March 5, 2014

የአገራችን መከላከያ ሰራዊት የበላይ አዛዦች የሰራዊቱ በጀት ይዘው እየጠፉ እንደሆነ ውስጥ አውቂዎች ከቦታው ገለፁ።



   በስርአቱ እምነት ያጡ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የበላይ መኮንኖች ለክፈለ-ሰራዊቱ ተብሎ የተመደው በርከት ያለ ገንዘብ እየያዙ በመጥፋት ላይ እንዳሉ የገለፀው መረጃው የ12ክፍለ ሰራዊት የፖለቲካና ቅስቀሳ ኦፐሬሽን ሃላፊ የሆነው ሌተናል ኮረኔል ተሾመ ተክለሀይማኖት አንዱ መሆኑንና ግለሰቡም ከክፍለ-ሰራዊቱ የበላይ አዛዦች ጋር በነበረው ያለመግባባት የተነሳ በየካቲት 3/2006 ዓ/ም የሰራዊቱ በጀት ይዞት እንደጠፋ የደረሰን መረጃ አስታወቀ።
   መረጃው በማስከተል ሌተናል ተሾመ ተክለሃይሞኖት ገንዘቡን ይዞት ከጠፋ በኋላ እስካሁን ድረስ የት እንዳለ ባለመታወቁ ምክንያት የክፈለ ጦሩ አዛዦች የኮረኔሉ የበታች አካል ሆኖ እየሰራ ለነበረው የክፍለ ጦሩ የፋይናንስ ሃላፊ ገንዘቡን ለምን ሰጠሀው በማለት በእስር ላይ እንደሚገኙ ለማወቅ ተችለዋል።