የትግራይ ክልል የፀጥታ
ክፍል ባለስልጣኖች ጥፋት ፈፅማቹሃል ብለው ከ8 ዓመት በላይ ከስራቸው አባርረዋቸው ለነበሩ የፖሊስ ሰራዊት አባላት አሁን ደርሰው
ሳያፍሩ ይቅርታ አድርግሉን ወደ ስራቹህ ተመለሱ እያሉ የጥሪ ደብዳቤ እየሰጡዋቸው መሆኑን የገለፀው መረጃው ይህንን ለማድረግ ያነሳሳቸው
ዋነኛ ምክንያትም አቅም ያላቸው ወደ ፖሊስ ሰራዊት ሊገቡ የሚችሉ ወጣቶች በማጣታቸው እየውሰዱት ያለ አማራጭ እንደሆነም የደረሰን
መረጃ አስታወቀ።
ከነዚህ ከ8 ዓመት በላይ ችግር አላቹህ በሚል ምክንያት ከስራቸው ተባርረው
የቆዩ ነገር ግን በአሁኑ ግዜ የይቅርታ ጥሪ ተደርጎላቸው የስራ ደብዳቤ የተሰጣቸው የፖሊስ አባላት በባድመ ከተማ የፖሊስ አባል
ሆኖ ሲሰራ የነበረ ነጋሲ መዓሾ፤ በሽሬ ከተማ እስር ቤት ውስጥ በምርመራ ክፍል ሲሰራ የነበረና ከበታው ተባርሮ ለረጅም ዓመታት
ታስሮ ከተፈታ በኋላ በቀን ስራ ላይ ተሰማርቶ የነበረ ለማ በርሀ
የተባለውና ሌሎች ያለተጠቀሱ እንደሚገኙባቸው ለማወቅ ተችለዋል።