Saturday, March 15, 2014

በትግራይ ማእከላዊ ዞን አሕፈሮም ወረዳ ውስጥ የሚገኙ አባወራዎች መኖርያ ቤታቹሁን አፍርሱ ተብሎው በስርአቱ ካድሬዎች እየተገደዱና እየታሰሩ መሆናቸው የተገኘው መረጃ አስታወቀ።



በመረጃው መሰረት እነዚህ በአህፈሮም ወረዳ ሰምሃል ቀበሌ የሚገኙ 35 የሚደርሱ አርሶ አደር አባወራዎች የወላጆቻቸው በሆነው መሬት ላይ የሰሩት መኖርያ ቤት አፍርሱት ተብሎው በቀበሌ አስተዳዳሪዎች እየተንገላቱና እየታሰሩ መሆናቸው ታውቋል።
በማስከተል ማንኛውም ነዋሪ የቤተሰቡን የእርሻ መሬት ይሁን ሃብት መውረስ ይችላል የሚል የስርአቱ መመርያ ቢኖርም ራሳቸው እያፈረሱት መሆናቸውና በዚህም መሰረት የ5 ልጆች አባት የሆኑ አቶ ገብረሃዋርያ ገብረስላሴ እንዳሉት ከቤተሰቦቼ ሆኜ ብዛት ያለው ገንዘብና ጉልበት አፍስሼ የሰራሁት ቤት ያለ መተክያና ካሳ ለማፍረስ ስላስገደዱኝ፤ ራሴ፤ ቤተሶበቼና ሌሎች ህፃናቶችና ሽማግሌዎች የሚገኙባቸው አያሌ ወገኖች መጠለያ በማጣታቸው ምክንያት በረሃ ላይ ተጥለን ለብርድና ለፀሃይ ተጋልጠናል ሲሉ ለምንጮቻችን ከሰጡት ሓሳብ ለማወቅ ተችሏል።