Saturday, March 15, 2014

ለፀረ ህዝብ የወያኔ-ኢህአዴግ አገዛዝ በመቃወም ወደ ትህዴን ድርጅት የተቀላቀሉ ወጣት ተማሪዎች በስርአቱ ውስጥ ያለዉ ብልሹ የመማር ማስተማር ሂደት የጎላ ችግር እንዳለው አጋለጡ።



እነዚህ በኢሮብ ወረዳ በሚገኙ የተለያዩ ትምህርት ቤቶች ሲማሩ የቆዩ ወገኖች በላያቸው እና በጓደኞቻቸው ላይ ሲፈፀም ለቆየው በደል ለማስወገድና ታግለው ስርአቱን ለመጣል ወደ ት.ህ.ዴ.ን ከተቀላቀሉ የተወሰኑትን ለመግለፅ፣-
-    ተስፋይ ገብረ ወልዱ
-    ብርሃነ ግርማይ ወልደሚካኤል
-    ጣዓመ ኪዳነ ተስፋይ
-    አንገሶም በየነ ሃጎስ
-    መርሃዊ ሃፍቶም ሃይለና ሊሎች ሲሆኑ እነዚህ ወጣቶች ከትግራይ ምስራቃዊ ዞን ኢሮብ ወረዳ ዓሊቴና ቀበሌ ወርአትለና እንዳልጌዳ ከተባሉ አካባቢዎች የመጡ እንደሆኑ ከትህዴን ማሰልጠኛ ማእከል የደረሰን መረጃ አመለከተ።
    ወጣት አንገሶም በየነ ከትህዴን ጎን ተስልፎ እንዲታገል ያስገደድው ምክንያት ሲያብራራ “በአካባብያቸው ትምህርት ቤት ባለመኖሩ ምክንያት ከቀበሌያቸው በጣም ርቆ በሚገኝ ትምህርት ቤት ተመላልሰው እንዲማሩ ስለሚገደዱ በመማር ማስተማር ሂደት ላይ ትልቅ እንቅፋት እንደሚገጥማቸው” ከገለፀ በኋላ የማታ ፈረቃ በሚሆንበት ግዜም ገራሳ በተባለው አካባቢ የሚገኙ የስርአቱ ወታደሮች  የት አመሻቹሁ፤ ከትህዴን ታጋዮች ግንኝነት ታደርጋላቹሁ እያሉ በጦር ሰፈራቸው አስረዉን ያድራሉ ሲል ብሶቱን ገልጸዋል።
    ወጣት ብርሃነ ግርማይ እና ተስፋይ ገብረ በበኩላቸው ከዩንጋ፤ ሒለና ደናይ ከሚባሉ ቀጠናዎች አካባቢ አብዛኞቹ ሴት ተማሪዎች የሚገኙባቸው ደዉሃን ወደሚገኘው ትምህርት ቤት ሄደው ለመማር ከሰዎስት ሰኣት በላይ ስለሚጓዙ ትምህርቱን ለማቋረጥ ተገደዋል ያለው መረጃው 9 ክፍል የደረሱ ተማሪዎች ቢሆኑም በአካባብያቸው ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ባለሞኖሩ ምክንያት ወደ አዲግራት፤ ደዉሃንና  ሌሎች ከተማዎች ሄደው በሚማሩበት ግዜ ለቤት ኪራይና ለሌሎች ኣላስፈላጊ ወጪዎች እየተጋለጡ በመሆናቸው ምክንያት ትምህርታቸው እያቋረጡ መሆናቸው ለማወቅ ተችለዋል።
    በመጨረሻ እነዚህ ወጣቶች ትምህርታችን አቋርጠን ወደ ትግል እንድንቀላቀል የመረጥንበት ምክንያት በስልጣን ያለው ገዢ ስርአት በህዝባችን ላይ እየፈፀመው ያለው በደል ሊያበቃ የሚችልው በትግል መሆኑን አውቀን ከትህዴን ጎን ተሰልፈን ለመታገል መርጠናል ሲሉ መናገራቸው በደረሰን መረጃ ለማውቅ ተችለዋል።