Saturday, March 15, 2014

በአማራ ክልል አዊ ዞን ውስጥ የሚገኙ የመንግስት ትምህርት ቤቶች በመማር ማስተማር ሂደት ላይ ችግር እንዳላቸው ተገለጸ።



በአዊ ዞን የሚገኙ የመንግስት ትምህርት ቤቶች በአፈፃፀም ላይ ችግር ስላላቸውና እየተሰጠ ያለው ትምህርት ጥራት የጎደለው በመሆኑ ምክንያት በአንከሻ ወረዳ ውስጥ የትምህርት ጥራት አስመልክቶ በተካሄደው ግምገማ ላይ ተማሪዎች ሊጨብጡት የሚገባቸው እውቀት ማግኘት እንዳልቻሉ ከቦታው በደረሰን መረጃ ለማወቅ ተችለዋል።
    የወረዳዋ የመንግስት ሰራተኞች ትምህርት ላይ እያጋጠመ ያለው ችግር አስመልክተው ግምገማ እንዳካሄዱና አንዳንድ ሰራተኞችም የችግሩ ዋናው ምክንያት የብአዴን ኢህአዴግ አባል በመሆኑ ብቻ ከፍተኛ ነጥብ ሲሰጠው አቅም ላለው ብቁ አስተማሪ ለሆነውና የስርአቱ አባል ላልሆነው ግን ዝቅተኛ ነጥብ እንደሚሰጠው ተገልፀዋል።
   ይህ በእንዲህ እንዳለ እየታየ ያለው የትምህርት ስራ አፈፃፀም ችግር መነሻው የስርአቱ የተዛባ ፖለቲካዊ አቅጣጫ ነው ብለው ለገመገሙ ሰራተኞች ከስራቸው እየተባረሩ እንደሆኑና በሌሎች የመንግስት መስራቤቶችም የተካሄደው የግምገማ ይዘትም ከዚሁ እንደማይለይ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ወገኖች አስታውቀዋል።