Friday, April 11, 2014

በሸራሮ ከተማ የሚገኙ የምግብ ቤቶችና ሸቀጣሸቀጦች ባለቤቶች ቫት አልቆረጣቹሁም ተብለው እየተቀጡ መሆናቸው ከአከባቢው የደረሰን መረጃ አስታወቀ።



በትግራይ ሰሜናዊ ምዕራብ ዞን ሸራሮ ከተማ የተለያዩ የንግድ ድርጅቶች ከፍተው በመስራት ላይ ያሉ ወገኖች የንብረት መሸጫ ፈፅማቹህ ስታበቁ ቫት አልቆረጣቹም እየተባሉ በቅጣት መልክ እጥፍ ገንዘብ ወደ መንግስት ገቢ እንዲያደርጉ የታዘዙ ዜጎቻችን ለዚህ ኢ-ፍትሃዊ አካየድ በመቃወማቸው ምክንያት ታስረው እንዲሰቃዩ መደረጉ ከከተማዋ የተገኘው መረጃ አስረድተዋል።
    በመረጃው መሰረት በሸራሮ ከተማ ለተገልጋዮቻችሁ ቫት አልቆረጣቹሁም ተብለው ከተቀጡ ባለሃብቶች አቶ ተከስተ በየነ የህንፃ መሳሪያ መሸጫ ባለቤት፤  አቶ ተከስተ የሳራ ሆቴል ባለቤት፤ አቶ አያሌው የምግብ ቤት ባለቤትና አቶ ሓጎስ የሸቅጣሸቆጦች ባለቤት እያአንዳዳቸው 17 ሺ ብር ጠቅላላ 68.000 ሺ ብር እንደተቀጡ ታውቀዋል።
   በተመሳሳይ አቶ ብርሃነ ሓድጉ የተባሉት የሸቀጣሸቀጥ ባለቤት። ለሁለተኛ ግዜ የደንበኞቻቸው ቫት ሳይቆርጡ በመስራት ላይ እያሉ ተይዘዋል በማለት  50 ሺ ብር እንደተቀጡና በዚሁ ልክ የሌለው ቅጣትም በከተማዋ የሚገኙ የንግድ ድርጅቶች ለኪሳራ ተጋልጠው የንግድ ቤቶቻቸው እንዲዘጉ ግድ እንደሆነባቸው መረጃው አክሎ አስረድተዋል።