Friday, April 11, 2014

በትግራይ ምዕራባዊ ዞን ቃፍታ ሑመራ ወረዳ የሚገኙ የመከላከያ አባላት ወርቅ ለቀማ ስራ ላይ ለተሰማሩ ወገኖች ከተቃዋሚ ድርጅቶች ጋር ትገናኛላቸሁ በሚል ሰንካላ ምክንያት እየደበደቡ ያጠራቀሙትን ወርቅ እየቀምዋቸው መሆኑን ተገለጸ።



እነዚህ ከተለያዩ የሃገራችን አካባቢዎች ወደ ቃፍታ ሑመራ እድሪስ ወደ ተባለው አካባቢ ወርቅ ለመልቀም የሄዱ ወገኖች ምንም አይነት ወንጀል ሳይፈፅሙ በአካባቢው በሚገኙ የኢህአዴግ መከላከያ ሰራዊት አባላት ለተቃዋሚ ድርጅቶች ትተባበራላችሁ በሚል ምክንያት የለቀሙትን ወርቅ በመንጠቅና በዱላ በመደብደብ መጋቢት 16 /2006 ዓ.ም ወደ ፖሊስ ጣብያ ወስደው እንዳሰርዋቸው ለማወቅ ተችለዋል።
በውቅቱ በዱላ ተደብድበው አካላቸውን ከተጎዱት ዜጎቻችን መካከል፣-
Ø ካሳሁን ደረጀ፤ ጥላሁን ታመነ፤አታክልቲ ይርዳውና ለግዜው ስሙ ያልታወቀውን ግለሰብ እጃቸውን የተሰበሩና በርከት ያሉ ወርቅ ለቃሚዎች ባልዋሉበት ወንጀል በቃፍታ ሁመራ ፖሊስ ጣብያ ውስጥ ታስረው እየተሰቃዩ እንደሚገኙ መረጃው አስታውቋል።
     በሃገራቸው ውስጥ በመስራታቸው ብቻ በስርዓቱ የመከላከያ ሰርዊት አባላት አካላቸውን የተጎዱና ለወራት ጉልበታቸውንና ላባቸውን አፍስሰው የለቀሙትን ወርቅ ተቀምተው በመታሰራቸው ልባቸው የቆሰሉ እነዝህ ወገኖች እስካሁን ድረስ የደረሰባቸውን በደል ወደ ፍርድ ቤት እንዳያቀርቡ ተከልክለው ፍርድ ቤት የሚባል ነገር ሂደው እንደማያውቁ መረጃው ጨምሮ አስረድትዋል።