Wednesday, April 9, 2014

በሑመራ ከተማ የሚገኙ ካድሬዎች የተለያዩ አስመሳይ ምክንያቶች በመፍጠር ነዋሪውን ህዝብ ገንዘብ አዋጡ እያሉ እያስገደዱት መሆናቸው ተገለፀ።



እነዚህ በትግራይ ክልል ምእራባዊ ዞን ሑመራ ከተማ ውስጥ የሚገኙ ካድሬዎች ለነዋሪዎች ለእስፋልት መንገድ ማሰርያ የሚውል ገንዘብ አዋጡ የሚል መመርያ ቢሰጥዋቸውም ህዝቡ ግን ከዚህ በፊት በተለያየ ምክንያት ያዋጣነውን ገንዘብ የት እንደደረሰ ሳናውቅ የምናዋጣበት ምክንያት የለም በማለት እንደተቃወሙ ከአካባቢው የደረሰን መረጃ አስታወቀ።
     መረጃው በማስከተል ለዚሁ ብሮጀክት ማስፈፀም የተሳናቸው የ ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ካድሬዎች አካሄዳቸውን በመለወጥ የቀድሞ የህወሃት ቪዲዮዎችን በማዘጋጀት ውድ በሆነ ዋጋ ህዝቡን እንዲገዛ እያስገደዱት መሆናቸውን መረጃው አክሎ አስረድተዋል።