Wednesday, April 9, 2014

በሰሜናዊ ምእራብ ትግራይ ዞን ታሕታይ አድያዎ ወረዳ ዓዲ ሃገራይ ቀበሌ ልዩ ቦታው ማይ አፃግእ አካባቢ የሚገኙ ወትሃደሮች ላአቅመ ሄዋን ያልደረሱ ሴቶችን እያስገደዱ መድፈራቸው ምንጮች ከቦታው ገለፁ።



በመረጃው መሰረት ዓዲ ሃገራይ አካባቢ ልዩ ቦታው አፃግእ ተብሎ በሚጠራው ቦታ የሚገኙ የከባድ ብረት( ሜካናይዝድ ) አባላት በአካባቢው በሚኖሩ ሰላማዊ ህዝቦች ላይ የተለያዩ አፀያፊ ተግባር እየፈጸሙ መሆናቸውና በምሳሌነት ደግሞ መጋቢት 1/2006 ዓ/ም ከተጠቀሰው ክፍል አባል የሆነው ጌቱ አማን የተባለው ወተሃደር ለአንድ ስምዋን እንድትጠቀስ ያልፈለገች የ11 ዓመት ልጃገረድ አስገድዶ ክብረ ንፅህናዋን የደፈራት መሆኑን ለማወቅ ተችለዋል።
    ይቺ የ6 ክፍል ተማሪ የሆነች ህፃን በደፈራት ወትሃደር በደረሰባት ከባድ ህመም ምክንያት አእምሮዋን በመሳት ሆስፒታል ገብታ በኣስጊ ሁኔታ ላይ የምትገኝ ስትሆን ባካባቢው ነዋሪ ህብረተሰብም በህፃንዋ ላይ በተፈፀመው አረሜናዊ ተግባር ተቆጥቶ “ እስከ መቼ ድረስ በወታደሮቹ ሚስቶቻችንና ሴት ልጆቻችን እየተደፈሩ የምንዋረደው፤ እስከመቼ ነው ሰላም አጥተን የምንነሮውና በስልጣን ላይ ያለው መንግስትስ ከችግሩ የማይታረመው የደርግ ወታደሮችስ ከዚህ የከፋ ስቃይ መቼ ፈፀሙብን! በማለት ቁጣቸውን በአንድ ድምፅ እያሰሙ መሆናቸውን መረጃው አክሎ አስረድተዋል።