Wednesday, April 2, 2014

የህወሓት ኢህአዴግ ባለስልጣናት በደጀና አካባቢ ልዩ ቦታ ማይ አድጊ ለሚኖር ህዝብ መሬት እንድንሰጣችሁ መጀምርያ ገንዘብ ክፈሉ ብለው አታለው ከወሰዱ በኋላ ገንዘቡን ልግላቸው እንዳደረጉት ተገለፀ።



ከአካባቢው በደረሰን መረጃ መሰረት በትግራይ ምዕራባዊ ዞን ወልቃይት ወረዳ ልዩ ቦታ ማይ አድጊ በሚባል አካባቢ በመሬት ማጣት የተቸገረው ህዝብ ከዞን በመጡ ከፍተኛ የስርዓቱ ባልስልጣናት መሬት የሌላችሁ ተደራጅታችሁ ለመንግስት ገቢ የሚሆን ገንዘብ አዋጥታጣችሁ ክፈሉና መሬት እንስጣቹሃለን ብለው ከተናገሩ በኋላ 40 የሚሆኑ ሰዎች ተደራጅተው ከ350 ሺ ብር በላይ አዋጥተው በየካቲት 20/2006 ዓ.ም ገንዘቡን ያስረከቡአቸው ሲሆን እነዚህ ባለስልጣናት ከዚህ በፊት ለሌላ ሰው የተሰጠ መሬት አድልዋቸው እንደተሰወሩ ታውቀዋል።
    እነዚህ ከአርሶ አዶሩ ህዝብ ከ350ሺ ብር በላይ ይዘው የተሰወሩ ባለስልጣናት በህጋዊ መንገድ የታደለ መሬት መሆኑን እያወቁ ነፃ መሬት ነው ብለው እንዳስረከቡዋቸውና ከተረከቡ በኋላ የሰው መሬት መሆኑን የተረዱ እነዚህ 40  ሰዎች አጭበርብረው የተያዘ መሬት በማደል ገንዘባቸውን የውሰዱባቸውን ባለስልጣናት በህግ ቁጥጥር ስር እንዲውሉ ጥረት ያደረጉ ቢሆኑም እንኳን ለነዚህ ወንጀለኞች ለመያዝና በህግ ፈት ቀርበው ተገቢውን ቅጣት እንዲያገኙ ለማድረግ እስካሁን ድረስ ትኩረት ሰጥቶ የሚንቀሳቀስ የፌደራል ይሁን የክልል ባልስልጣን እንደሌለና እነዚህ የችግሩ ሰለባ የሆኑ ዜጎችም ለከባድ ችግር ተጋልጠው እንደሚገኙ ለማወቅ ተችልዋል።
   የግል ሃብት ለማካበት ሲሉ ይህንን አስነዋሪ ተግባር ከፈፀሙ ባለስልጣናት ውስጥ የዞኑ ምክትል አስተዳዳሪና የመሬት ልማት ሃላፊ አቶ ወለንሳና  በዞኑ የመሬት ልማትና ቁጥጥር ሃላፊ የሆነው አቶ ላአከ ሲሆኑ በተጨማሪም ከነሱ ስር ሁነው ይህንን እኩይ ተግባር የፈፀሙ ክብሮም ለማና ወዲቀሺ የተባሉ እንደሚገኙባቸውም ለማወቅ ተችልዋል።