Monday, June 30, 2014

በአብደልራፍዕ ከተማ የሚኖርና በቀን ስራ ላይ ተሰማርቶ እየሰራ የነበረው ግለሰብ 200 ብር አልከፈልክም ተብሎ ከታሰረ በኋላ ሰኔ 15 /2006 ዓ/ም እስር ቤት ውስጥ እንደተገደለ ታወቀ፣፣



በአብደልራፍዕ ከተማ የሚገኙ አስተዳዳሪዎችና ፖሊሶች በቀን ስራ ላይ ለተሰማሩ ሰራተኞች ስራ ላይ ውለው ወደ ቤታቸው ሲመለሱ መንገድ ላይ ጠብቀው 200 ብር እንዲከፍሉ በማስገደድ እንደሚያስሯቸው የገለጸው መረጃው ከታሰሩት መካከልም አስራት ማስረሻ የተባለው ወጣት 200 ብር መክፈል አልችልም ብሎ ወደ እስርቤት ከሄደና ከእስርቤቱ በሌሊት አውጥተው ሲደበድቡት ለማምለጥ በሞከረበት ሰአት ሳጅን አወቀ ክንዱ የተባለው ፖሊስ ቶኩሶ እንደገደለው ለማወቅ ተችሏል፣፣
     መረጃው ጨምሮ እንደገለፀው በአስተዳዳሪዎቹና በፖሊሶቹ ተግባር የተቆጣ የአብደራፍዕ ከተማ ህዝብ ላቡን አፍስሶ የሚኖር ንፁህ ዜጋ 200 ብር መክፈል አልችልም በመለቱ ብቻ እንዲገደል መደረጉ ሰብአዊነት የሌለው ተግባር ነው ሲሉ ብሶታቸውን እየገለፁ መሆናቸውን መረጃው አክሎ አስረድቷል፣፣