Monday, June 30, 2014

በዳንሻ አከባቢ “ሂወት የእርሻ መካናይዜሽን “ ተብሎ በሚጠራው የህወሃት ድርጅት ሂሳብ ሹም ሆኖ ሲሰራ የነበረ አቶ ናስር 2 ሚልዮን ብር ይዞ እንደጠፋ ምንጮቻችን ከአከባቢው አስታወቁ፣፣



በምንጮቻችን መረጃ መሰረት በትግራይ ምእራባዊ ዞን ዳንሻ አከባቢ በሚገኘው ሂወት መካናይዜሽን ድርጅት ሂሳብ ሹም ሆኖ ሲሰራ የነበረ አቶ ናስር 135 የሚል የሂሳብ ቁጥር ቼክ ተጠቅሞ ጎንደር ከተማ ከሚገኘው የወጋገን ባንክ ሰኔ 13 / 2006 ዓ/ም ለ500 ኩንታል እህል መግዣ ተብሎ የተፈቀደ 2 ሚልዮን ብር አውጥቶ ይዞት እንደጠፋ ለማወቅ ተችሏል፣፣
    የህወሓት ድርጅት በህዝብና በሃገር ስም ከሚነግዱት ግለሰቦች እየተጠቀሙበት ካሉ ሂወት የእርሻ መካናይዘሽን ገንዘብ ይዞ ለተደበቀው ናስር ለመፈለግ የፀጥታና የደህንነት አባላት ቢሰማሩ እንኳን ሊያገኙት እንዳልቻሉና ግለሰቡ ገንዘቡን ይዞ ከሃገር ወጥቶ ሊሆን እንደሚችል የብዙ ወገኖች ግምት መሆኑን ምንጮቻችን ጨምረው አስረድተዋል፣፣