Monday, June 30, 2014

በአስገደ ፅንብላ ወረዳ፤ እንዳባጉና ከተማ ውስጥ የሚገኙ የስርአቱ ካድሬዎችና አስተዳዳሪዎች የከተማዋን ህዝብ አስገድደው ሰኔ 14/2006 ዓ/ም የድጋፍ ሰላማዊ ሰልፍ እንዲያደርግ መመሪያ ቢሰጡትም ህዝቡ እንደተቃወመው ምንጮቻችን ከቦታው አስታወቁ፣፣



በሰላማዊው ሰልፍ ወቅት የነበሩ ምንጮቻችን እንደገለፁት ለእንዳባጉና ከተማ ነዋሪ ህዝብ በወረዳችን ውስጥ መልካም አስተዳደርና ፍትህ ተረጋግጠዋል በማለት ድጋፋችው በሰላማዊ ሰልፍ ለመግለፅ በስርአቱ ካድሪዎች አስገዳጅነት ወደ ከተማው እንዲወጡ መደረጉንና ህዝቡ በተሰበሰበበት ቦታ ካድሬዎች ስለ መልካም አስተዳደርና ፍትህን በሚመለከት ቅስቀሳ በጀመሩበት ሰአት በስብሰባው የተገኘው ህዝብ ፍትህ እንዲሰፍን አድርገናል ከምትሉን ፍትህን ጨርሶ እንዳይኖር ተንቀሳቅሰናልና ቀብር ላይ ተሳተፉ ብትሉን ይሻላል፤ ፍትህና መልካም አስተዳደር ለማምጣት ጥረት ከምታደርጉ ይልቅ ገንዘብ የምታገኙበት ብልሃት በማፈላለግ ነው ግዜአችሁን የምታጠፉት ካሁን በኋላም ከናንተ የምንጠብቀው በጎ ነገር የለም በማለት ተቃውማቸውን እንደገለፁ ለማወቅ ተችሏል፣፣ 
     ተገደው በስብሰባው ላይ ከተገኙና ለስርአቱ ብልሹ አሰራር ከተቃወሙት አንዱ።- አቶ አታክልቲ ደሳለኝ የተባሉት ቀደም ብለው የብረታ ብረት ድርጅት የነበራቸውና በስርአቱ ህገ ወጥ የግብር አከፋፈል ለኪሳራ በመጋለጣቸው ምክንያት ድርጅታቸውን እንዲዘጉ የተገደዱ የ02 ቀበሌ ነዋሪ መሆናቸውን ለመረዳት ተችሏል፣፣