Monday, June 30, 2014

የወያኔ ኢህአደግ ስርአት ካድሬዎች በትግራይ ሰሜናዊ ምእራብና ምእራብ ዞኖች ሚገኑ ወጣት ተማሪዎች ወደ ውትድርና ግቡ እያሉ ቀጣይ እየቀሰቀስዋቸው እንዳሉ ታወቀ፣፣



በሰሜናዊ ምእራብና ምእራብ ትግራይ ሚገኙ ወጣት ተማሪዎች ወደ ውትድርና ተነሱ እየተባሉ በስርአቱ ካድሬዎች ቅስቀሳ እየተደረገላቸው እንዳሉ ከገለፀ በኋላ የቅስቀሳው ትኩረት ደግሞ የ10ኛ ክፍል ተማሪዎችና ከዛ በላይ የሆኑት የትግርኛ ተናጋሪዎች ሲሆን ለኩናማ ተናጋሪዎች ደግሞ ከ7ኛ በላይ ለሚማሩ የሚል እንደሆነ የደረሰን መረጃ አመለከተ፣፣
     ይህ ወደ ውትድርና የሚል ቅስቀሳ በሑመራና አከባቢዋ እንዲሁም በሽሬና ሸራሮ ከተሞችና ሌሎች ወረዳዎች በሰፊው መንገድ እየተካሄደ መሆኑን የገለፀው መረጃው የወያኔ ኢህአደግ ባለስልጣናት ቅስቀሳውን እንዲካሄድ ያስገደዳቸው ምክንያት በውትድርና ሆኖ የስልጣናቸው እድሜ እያስረዘመላቸው የቆየ ሰራዊት ትቷቸው እየጠፋ ባለበት በአሁኑ ግዜ የስልጣናቸው ቀጣይነት በአደጋ ውስጥ እንደሚገኝ ስለ ተገነዘቡ ለዚ መተኪያ እንዲሆናቸው በሚል የፈጠሩት ደባ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፣፣