Tuesday, July 8, 2014

በትግራይ ማዕከላዊ ዞን ዓድዋ ከተማ ውስጥ የሚገኙ ነጋዴዎች ከአቅማቸው በላይ የሆነ ግብር እንዲከፍሉ በመገደዳቸው ምክንያት ለኪሳራ መጋለጣቸውን ምንጮቻችን ከቦታው አስታወቁ።




    እነዚህ በአድዋ ከተማ ውስጥ በንግድ ስራ ተሰማርተው ቤተሰባቸውን ሲያስተዳድሩ የቆዩ ነጋዴዎች ፍትሃዊነት የሌለው ግብር እንዲከፍሉ እየተገደዱ መሆናቸውን የገለፀው መረጃው በተለይ በትናንሽ ሸቀጣ ሸቀጦች፤ መጠጥ ቤትና በሌሎች የንግድ ስራ ላይ ለተሰማሩ ወገኖች በላያቸው ላይ ወገናዊነት በተጠናወተው መንገድ እየተፈፀመ ያለው የግብር አከፋፈል ስርዓት እንዲሻሻልላቸው በማለት ፋይላቸውን በማቅረብ የይግባኝ ጥያቄ እያቀረቡ መሆናቸውን የደረሰን መረጃ አስረድቷል።
    ከአቅማቸው በላይ ግብር እንዲከፍሉ ከተገደዱትና በዚህም ምክንያት ብሶታቸውን እየገለፁ ካሉ ወገኖች መካከል።-
-                      አቶ ገብሩ አበበ 22,578 ብር
-                      አቶ ጉዕሽ ገብረስላሴ 28,950 ብር
-                     ወ/ሮ ዝማም በየነ ተሰማ 14,490 ሶስቱም የሆቴል ባለቤቶች
-                    አቶ ስዒድ ሙስጦፋ የሸቀጣ ሸቀጥ ነጋዴ 38,990 ብር
-          አቶ ገብረሂወት ወለኺዳን የቤት እቃና የእርሻ መሳርያ ሱቅ ባለቤት 25,760 ብር
-                   ወ/ሮ አስካሉ አለምብርሃን 6,700 ብር
-                    አቶ ዮውሃንስ ሃይሉ 5.771 ብር ሁለቱም ባለ ምግብ ቤቶች
-            አቶ ደስታ ገብረዝጊአብሄር የፀጉር መስተካከያ ባለቤት 2,545 ብር እንዲከፍሉ የተጠየቁ ሲሆኑ ሌሎች በርካታ ነጋዴዎችም ፋይላቸውን በመያዝ ይግባኝ እየጠየቁና ድርጅታቸውን እንዲዘጉ እየተገደዱ መሆናቸውን መረጃው አክሎ አስረድቷል።