Tuesday, July 8, 2014

በትግራይ ምዕራባዊ ዞን በሁመራ ከተማ የቴሌኮምኒኬሽን ሰራተኛ የነበረው ግለሰብ የስርዓቱን ብልሹ አሰራር በመቃወም የድርጅቱን ገንዘብ ይዞ መሰወሩን ምንጮቻችን ከከተማው አስታወቁ።




በሁመራ ከተማ በቴሌኮምኒኬሽን ፅ/ቤት ውስጥ ሲም ካርድና የሞባይል  ካርድ በመሸጥ ስራ ላይ ተመድቦ ሲሰራ የቆየ እዮብ የተባለው ሰራተኛ ሰኔ 20/2006 ዓ/ም ከአንድ መቶ ሺ በላይ ገንዘብ ይዞ መሰወሩን የተገኘው መረጃ አስታወቀ።
     መረጃው በማስከተል አቶ እዮብ በቴሌኮምኒኬሽን ፅ/ቤት ውስጥ በቆየበት ግዜ በወያነ ኢህአዴግ ባለስልጣናት ግቦኝነትና አድልዎ እየተፈፀመ መሆኑን፤ በግለሰብ ደረጃ ይሁን በድርጅቶች የሚተላለፍት መልእክቶች በስርአቱ ልዩ መሳርያዎች እየተጠለፉ የህዝቡን ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች እየተጣሱ መሆናቸውና ለሰራተኛው ተገቢ ደመወዝ እየተከፈለው እንዳልሆነ በተደጋጋሚ ሲገልፅ መቆየቱንና ለዚህ ተግባር በመቃወምም እርምጃውን እንደወሰደ ለማወቅ ተችሏል።