በመረጃው መሰረት በትግራይ ምእራባዊ ዞን በረከት አከባቢ ከሚኖሩ አንዱ
የሆነው ተስፋይ ገብረዝጊሄር የተባለ አርሶ አደር በህጋዊ መንገድ በተሰጠው የእርሻ መሬት የዘራው ሰሊጥ የሱዳን ሰራዊት ወደ አከባቢው
በመምጣት “ለምን እዚህ አካባቢ እህል ትዘራለህ” ብለው በማስፈራራት የሰሊጥ ቡቃያውን ነሓሴ 1 / 12 / 2006 ዓ/ም ሙሉ በሙሉ
ገልብጠው ማሽላ እንደዘሩት መረጃው አስታውቋል።
ይህ በርካታ ገንዘብ ወጭ ተደርጎበት የተዘራውን ሰሊጥ በሱዳን ሰራዊት
ተገልብጦ ከጥቅም ውጭ በመሆኑ ምክንያት የእርሻው ባለቤት ለሚመለከታቸው አካላት አቤቱታውን ካቀረበ በኋላ ወደ አካባቢው ከበረከት
የሄዱ የምልሻ አባላትና የሱዳን ሰራዊት ጋር በተከሰተ ግጭት አምሳሉ የተባለው የምልሻ ሃላፊና አንድ ስቪል ሰራተኛ መቁሰላቸውና
በአከባቢው አሁንም ከባድ ውጥረት ሰፍኖ እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል።
ከዞኑ ሳንወጣ በዓዲ-ጎሹ አከባቢ የሚገኙ 300 የሚሆኑ አርሶ አደሮች
ለአስርት አመታት ያክል ያረሱትን መሬታቸው በቃፍታ ሑመራ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ዮሃንስ አከባቢው ለደን ልማት የተከለለው ማን እረሱት
አላችሁ በማለት በቅሎ በደህና ሁኔታ የነበረውን ሰሊጣቸውን መድሃኒት ረጭተው እንዲጠፋ እንዳደረጉት ተገለፀ እኒህ ከ300 በላይ
የሆኑ አርሶ አደሮች ከጅምሩ ገንዘባችንና ጉልበታችንን ሳንከስር ለምን አቁሙት አልተባልንም ቀጣይ ህይወታችንን በምን ልንመራ ነው።
ሲሉ አቤቱታቸውን ቢያቀርቡም ሰሚ እንዳላገኙ መረጃው ጨምሮ አስረድቷል።