Monday, August 25, 2014

በትግራይ ማዕከላዊ ዞን ቆላ ተምቤን ወረዳ የመላቅመ ቀበሌ ነዋሪዎች ከሚኖሩበት ቀያቸው በአካባቢው አስተዳደር እንዲፈናቀሉ እየተገደዱ መሆናቸውን ከአካባቢው የሚገኙ ምንጮቻችን አስታወቁ።



እነዚህ የቆላ ተምቤን የመላቅመ ቀበሌ ነዋሪዎች በህጋዊ መንገድ መሬት ተረክበው እርሻና ወርቅ እየለቀሙ ለአመታት ሲኖሩበት ከነበረው መሬታቸው እንዲፈናቀሉ በአካባቢው አስተዳዳሪ ትእዛዝ የተሰጣቸው ቢሆኑም የአካባቢው ነዋሪዎች ግን የወረደውን ትዕዛዝ ስላልተቀበሉት በአስተዳዳሪውና በህዝቡ መካከል ከባድ ንትርክ ተፈጥሮ እንደሚገኝ ምንጮቻችን ከአካባቢው በላኩት መረጃ ሊታወቅ ተችሏል።
   ይህ በእንዲህ እንዳለ በትግራይ ሰሜናዊ ምዕራብ ዞን፤ በሽራሮ ከተማ አጋጥሞ ባለው  የመጠጥ ውሃ እጥረት ምክንያት የከተማዋ ነዋሪዎች ለከባድ ችግር ተጋልጠው እንደሚገኙ የገለፀው መረጃው ከሩቅ አካባቢ ተጉዘው የሚያመጡት ውሃም ቢሆን ጥራቱን የጠበቀ ባለመሆኑ የተነሳ የአካባቢው ማህበረሰብ ለተለያዩ ውሃ ወለድ በሽታዎች ተጠቂ እየሆነ እንደሚገኝ በተደጋጋሚ ስንገልፅ መቆየታችን የሚታወስ ነው።