በምንጮቻችን መረጃ መሰረት
የህወሓት ከፍተኛ ባለስልጣኖች ከሃምሌ 25 እስከ ነሐሴ 8 /2006/ዓ,ም የኲሓን ከተማን ጨምሮ ከስድስቱም የመቐለ ክፍለ ከተሞች ተወክለው ለመጡ የህወሓት
የበታች አመራሮችና ካድሬዎቻቸው በማስጠራት በስብሰባ ላይ ጠምደዋቸው እንድሰነበቱ የገለጸው መረጃው የስብሰባው አጀንዳም ሰለመልካም
አስተዳደር’ና ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅት የሚመለከት እንደነበረ ለማወቅ ተችሏል።
በአይደር ክፍለ ከተማ ለሁለት ሳምንታታ ያህል ሲካሄድ በሰነበተው ስብሰባ
ላይ የነበሩ ዝርዝር አጀንዳዋች በክፍለ ከተሞቹ ያሉት የፀጥታ አባላት በያሉበት ክፍለ ከተማ ጠንክረው መጠበቅ እንዳለባቸው፤ ለማያውቁት
ሰው ቤት ማከራየት እንደማይገባቸውና ይዘው ወደ ቀበሌ ማምጣት እንደሚኖርባቸው የሚሉና ሌሎች በስባሰባው ላይ የተነሱ አጀንዳዎች
እንደሆኑ፤ ይህም ስርዓቱ ምን ያህል በጭንቀትና በፍርሓት ተውጦ እንዳለ
የሚያመላክት ነው ሲሉ በስብሰባው ላይ የተሳተፉ አካላት መግለፃቸውን
ምንጮቻችን ገልፀዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በስብሰባው ላይ የተስተፉ የህወሃት ማሌሊት አባላት’ና
ካድሬዎች ብዛታቸው 1005 እንደሆኑና ከቅርብ ለመጡ 200ብር ውሎ አበል ሲከፈላቸው፤ ራቅ ካለ ክፍለ ከተማ ለመጡ ደግሞ 600ብር
እንደተከፈላቸው የተገኘው መረጃ አክሎ አስረድተዋል።