Wednesday, August 20, 2014

በማይ ካድራና አደባይ ሌሎች አካባቢዎች የሚገኙ የቀን ሰራተኞች በፖሊስ እየተገደዱ ወልቃይት ወደ ሚገኘው የስኳር አገዳ እርሻ እየተወሰዱ መሆናቸውን ከአከባቢው የደረሰን መረጃ አስታወቀ።



በትግራይ ምእራባዊ ዞን ማይ ካድራና አደባይ ሌሎች ከተማዎች በቀን ስራ ላይ ተሰማርተው ህይወታቸውን በመምራት ላይ የቆዩትን ወገኖች ባሁኑ ግዜ በዞኑ ውስጥ የሚገኙ ፖሊሶች ወልቃይት ወደ ሚገኘው የስኳር አገዳ እርሻ በሃይል አስገድደው በመውሰድ ጉልበታቸውን እየበዘበዙት መሆናቸውን የገለፀው መረጃው አንሄድም ብለው ለተቃወሙትም የማንነት መታወቅያቸው እየተነጠቁ ወደ ትውልድ አገራቸው እንደሚባረሩ ማስጠንቀቅያ እንደተሰጣቸው ለማወቅ ተችሏል።
   እነዚህ ወገኖች ቀደም ሲልም በስርአቱ ተላላኪዎች ወልቃይት ወደ ሚገኘው የሰሊጥ እርሻ ላይ ተገደው ለአረም ስራ መወሰዳቸውና የሰሩበትን ዋጋ ባለመከፈላቸው ተቃውሞ ማሰማታቸው የሚታወቅ ሆኖ አሁንም እንዳለፈው በነፃ ጉልበታችን ለመጠቀም እየተደረገ ያለው እኩይ ተግባር ነው ሲሉ ምሬታቸውን በመግለፅ ላይ መሆናቸው መረጃው አክሎ አስረድተዋል።