Monday, August 25, 2014

የአዲስ አበባ ነጋዴዎች የገበያ ዋጋ እንዲንር የተቃዋሚዎች ስራ እያሳለጣችሁ ናችሁ በሚል ምክንያት በአስተዳደሩ የንግድ ድርጅታቸው እየታሸገ መሆኑን ምንጮቻችን አስታወቁ።



በመረጃው መሰረት በአዲስ አበባ ዙሪያ ባሉት ክፍለ ከተሞች የሚገኙ ነጋዴዎች የተቃዋሚ ፓርቲ ተልእኮ ተቀብላችሁ በመተግበር ገበያ እንዳይረጋጋና በሸቀጦች ዋጋ ጭማሬ በማድረግ መንግስት ለሰራተኞች ያደረገውን የደሞዝ ጭማሬ መነሻ በማድረግ ፀረ መንግስት ተቓውሞ እንዲነሳሳ ታደርጋላችሁ በሚል ከሃቅ የራቀ ምክንያት የቡዙዎችን ነጋዴዎች ድርጅታቸው በስርኣቱ እንደተዘጋ ታወቋል።

    የታሸጉት ሱቆች ብዛትም ወደ 1500 በላይ ሲሆኑ ይህ ተግባርም በአዲስ አበባ ብቻ እንዳልሆነና  በሁሉም የሃገራችን ከተሞች ጭምር በከፋ መልኩ እየቀጠለ እንዳለ ምንጮቻችን አስረድተዋል።