በመረጃው መሰረት እኒህ በላይና በታች ጋይንት ወረዳዎች የሚገኙ ነዋሪዎች ያላቸውን የቤት እጥረት
ለመቅረፍ ከአመታት በፊት ወደ ማዘጋጃ ቤት ያቀረቡትን ጥያቄ ሊፈታላቸው ስላልቻለ በስርዓቱ ላይ ምሬታቸውን እየገለፁና ለቤት መስሪያ
እንዲውል በማሰብ ቆርጠው ያስቀመጡት አጠናዎች ብዙ ጊዜ ከመቆየቱ የተነሳ ከጥቅም ውጭ እንደሆነ ታወቋል።
በተመሳሳይ በወረዳዎቹ የተሟላ መሰረተ ልማት ስለሌለ በውጤቱም የንግድ
ባለቤቶች ለኪሳራ መጋለጣቸውን የገለጸው መረጃው በተለይም መብራት ሃይል ለብዙ ቀናት ስለ አቛረጠ ነዋሪዎች በእለታዊ ኑሮአቸው ላይ
ከባድ ችግር እያጋጠማቸው መሆናቸውን መረጃው ጨምሮ አስረድቷል።