በመረጃው መሰረት ገበያን
ለማረጋጋት ተብሎ በአዲስ አበባ ከተማ በተከፈቱ ሱቆችና መጋዝኖች የሚገኝ ንብረት የስርአቱ ባለስልጣኖች በተመጣጣኝ ዋጋ ለተጠቃሚው
ህዝብ እንዲከፋፍል ተብሎ የመጣውን ንብረት ከነሱ ጋር ለሚተባበበሩ ሃብታሞች በስጠታቸው ምክኒያት በሌሎች ወገኖች ላይ ቅሬታና ተቃውሞ
ማጋጠሙ ለማወቅ ተችሏል።
መረጃው ጨምሮ እንደገለፀው የኢህአዴግ ስርአት በብዙሃን መገናኛ ለህዝቡ
በቂ አቅርቦት እያዘጋጀሁ ነኝ ብሎ ቢናገርም ሃቁ ግን ለፖለቲካ ፍጆታ ከመሆን አልፎ በህዝቡ ላይ ያመጣው ለውጥ እንደሌለና በአቅርቦት
እጦት ምክንያት ከባድ ችግር ላይ መውደቁን መረጃው አክሎ አስረድቷል።