Wednesday, August 20, 2014

የመልካም አስተዳደር እጥረት በፈጠረው ችግር እየተሰቃዩ ያሉ የምዕራብ ሸዋ ዞን ዳርጌ ወረዳ ነዋሪዎች ያጋጠማቸውን ችግር በሰላማዊ ሰልፍ እንዳይገልፁ በስርዓቱ የተለያዩ ሴራዎች እየተፈጠሩባቸው መሆኑ ተገለፀ።



   በምንጮቻችን መረጃ መሰረት በኦሮሚያ ክልል፤ ምዕራብ ሸዋ ዞን፤ ዳርጌ ወረዳ በመልካም አስተዳድር እጥረት ምክንያት የመሰረተ ልማት ችግር በሰፊው መኖሩን በመግለፅ በተለይ በዜጎች ዕለታዊ እንቅስቃሴ ላይ ወሳኝ የሆኑ እንደ ውሃ፤ መብራት፤ መንገድና የጤና ኬላ የመሳሰሉት በአካባቢው ስላልተዘረጉ ነዋሪው ህዝብ ችግሩን በሰላማዊ ሰልፍ  ለመግለፅ ለመጪው እሁድ ነሃሴ 18/ 2006 ዓ/ም ለማካሄድ ዝግጅት እያደረጉ ባሉበት የወረዳው አስተዳዳሪዎች ሌሎች አካባቢዎች እንዳይሰሙ ኔት-ዎርክ እንደዘጉባቸው ለማወቅ ተችሏል።
   ምንጮቻችን ጨምረው እንደገለፁት የአካባቢው መላው ህዝብ ከራሱ የሚጠበቁ እንደ ግብር መክፈልና የመሳሰሉትን ስራዎች የሚፈፅም ቢሆንም በሙስና የተጨማለቁ የስርዓቱ አስተዳዳሪዎች የመልካም አስተዳደርን ሙሉ በምሉ በማጥፋት ለልማት ተብሎ የተበጀተ ገንዘብ ለግል ጥቅማቸው እያዋሉ በአካባቢው በተከታታይ የሚነሱ የመሰረት ልማት ጥያቄዎችን ሊመልሱ ባለመቻላቸው የተቆጣው ህዝብ በስርዓቱ ላይ የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ ለማካሄድ በማሰቡ ይህንንም ለማደናቀፍም የደህንነት ካድሬዎች ለአንድ ሳምንት ያህል ኔት-ዎርክ እንደዘጉ ታውቋል።