Saturday, September 20, 2014

በአዲስ አበባ ከተማ ለሚገኙ ከ300 መቶ በላይ ለሚሆኑ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ስኬታማ ስብሰባ አካሄጃለሁ እያለ የወያኔ ኢህአዴግ ገዥው መደብ እየተናገረ ያለው ከእውነታው የራቀ እንደሆነ በስብሰባው ላይ የተሳተፉትን ተማሪዎች መሰረት በማድረግ ምንጮቻችን የላኩልን መረጃ አስታወቀ።



   በመረጃው መሰረት በዚህ የክረምት ወር ከተለያዩ የሃገራችን ከከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ላይ በገዢው መንግስት ሲካሄድ የሰነበተው ስብሰባ ስኬታማ በሆነ መንገድ እንደተጠናቀቀ በሚዲያዎቹ እየገለፀ ያለው ህወሃት ኢህአዴግ በፍፁም ከእውነታው የራቀና በጥቂት እሱን መስለው በሚንቀሳቀሱ ሰዎች የተነገረ እንደነበር የገለፀው መረጃው እነዚህ የስርዓቱ ደጋፊዎች በመድረኩ የተኑስትን ጥያቄዎችና ሂሶች እንዳልነበሩ አድርገው ማለፋቸውን የታዘቡ አብዛኛው ተማሪዎች ለምን በመድረኩ የተነሱት ጥያቄዎችና ሂሶች በትክክል ለህዝቡ እልቀረቡም በማለት በስርዓቱ ላይ ተቃውሞአቸውን እየገለፁ መሆናቸውን ተገልፀዋል።
   ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው መድረኩ ላይ ተሳታፊ በነበሩ ተማሪዎች ለተነሱ የተላያዩ ጥያቄዎች፤ አስተያይቶችና ጠንካራ ክርክሮች  የወያኔ ኢህአዴግ ገዢው ስርአት ተገቢውን ምላሽ እንዳልሰጠባቸውና ውሸትን እውነት አስመስሎ በሚዲያ ማስተላልፉም የስርዓቱ ዋነኛ መለያ ባህሪ እንድሆነ ተማሪዎቹ በስፋት እየገለፁት እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል።