Saturday, September 20, 2014

በቃፍታ ሁመራ ወረዳ በረከት ቀበሌ የሚገኙ ሁለት ኮሚቴዎች ከህዝብ እያጭበረበሩ ገንዘብ በመቀበላቸው ምክንያት ህብረተሰቡ ምሬቱን እያሰማ እንደሚገኝ ምንጮቻችን ከከተማዋ ገለፁ።



   በምንጮቻችን መረጃ መሰረት በበረከት ከተማ አስተዳደር ውስጥ ሁለት   ኮሚቴዎች የተቋቁሙ ሲሆን የነዚህ ሁለት ኮሚቴ ሃላፊዎችም የስርዓቱ ካድሬዎች በመሆናቸው የተነሳ ከህዝብ የሰበሰቡትን ገንዘብ ለከተማዋ ልማት ማዋል ሲገባቸው  ገንዘቡን ልግል ጥቅማቸው እያደርጉት እንደሚገኙ መረጃው አስታውቀዋል።
በሁኔታው የተማረረው የከተማዋ ነዋሪ ህዝብ በበኩሉ ለከተማችን ልማት ብለን ያዋጣነው ገንዘብ እዚህ ገባ ሳይባል በሃላፊዎች እየተጠፋፋ ነው በማለት የተቓቓሙትን ኮሚቴዎች ቢከሱም በሓላፊዎች ላይ የከተማዋ አስተዳደር ምንም አይነት እርምጃ እንዳልወሰደና የህብረተሰቡን ክስ የተቀበሉ ላማስመሰል ግን ሃይለ ገብረገርግስ ለተባለ ግለ ሰብ ይዘውት እንደሚገኙ ምንጮቻችን ከበረከት በላኩልን መረጃ ለመረዳት ተችሏል።