በምንጮቻችን መረጃ መሰረት በአማራ ክልል ጎንደር ከተማ ቀበሌ 08 የሚገኙ
የፖሊስ ኮሚኒቲ አባላት በንፁሃን ዜጎች ላይ በደል እያወረዱ መሆናቸውን
በመግለፅ ይህንን ወንጀል እየፈፀሙ ያሉትን የፖሊስ አባላት የሚያማክላቸው ደግሞ ሳጅን ተስፋዬ ኩንሳ መሆኑን የገለጸው መረጃው ይህ
የፖሊስ ኮሚኒቲ አዛዥም ኩራቴ በለጠ ለተባለው ንፁህ ዜጋ ምንም አይነት የፈፀመው ወንጀል ሳይኖረው በአይን ጥርጣሬ ብቻ አስሮት
ከቆየ በኋላ ህግ ጥሶ ሊያመልጥ መኩሮዋል በሚል ተጨባጭነት በሌለው ምክንያት ጳጉሜን 1 2006 ዓ/ም በጥይት ተኩሶ እንደገደለው
ምንጮቻችን ገለፁ።
ይህ በወያኔ
ኢህአዴግ ፖሊሶች በንፁሃን ዜጎች ላይ እየተፈፀመ ያለው የማሰርና የመግደል ወንጀል በጎንደር ከተማ ብቻ ሳይሆን በሁሉም የሃገራችን
አካባቢዎች እየተካሄደ ያለ ርህራሄ የሌለውና ሰብአዊነት የጎደለው ተግባር እንደሆነ በብዙ ሰዎች እየተነገር እንደሚገኝ መረጃው አስርድቷል።