Thursday, September 18, 2014

የአዲግራት ከተማ ጎዳናዎች መብራት ስለሌላቸው በሌሊት ወደ-ስራ ለሚንቀሳቀሱ የህብረተሰብ ክፍሎች ችግር ላይ የጣላቸው መሆኑንና የአንዳንድ ተቋማት ባለቤቶችም ንብረታቸው እየተዘረፈ እንደሚገኝ ተገለፀ።



   በመብራት ማጣት ምክንያት እየተሰቃዩ ካሉ የሃገራችን ከተሞች መካከል አንዷ የሆነችው የአዲግራት ከተማ የከተማዋ ነዋሪዎች በሌሊት ወደ ሥራ በሚሄዱበት ሰዓት በዘራፊዎች እየታፈኑ ንብራታቸው እየተሰረቀ እንደሚገኝ መረጃው አስትውቋል።
   በዚህ የመብራት እጥረት ምክንያት ለችግር ሰላባ  ከሆኑት ዜጎች መካከልም አንድ ቄስ ቤተክርስትያን እየሄዱ በነበረበት ሰዓት ማንነታቸው ያልታወቁ ሰዎች ጨለማን ተገን በማድረግ በላያቸው ላይ አደጋ አድርሰው ማምለጣቸውና እስካሁን ድረስም በነዚህ ሰዎች ላይ ምንም አይነት ክትትልም ሆነ ምርመራ እንዳልተደረገ የደረሰን መረጃ ገልጿል።