Thursday, September 18, 2014

በአብ-ደራፊዕ አካባቢ ፀጥታ ለማስከበር ተብለው የተሰማሩትን የፌደራል ፖሊስ አባላት የቀን ሰራተኞችን ገንዘብ አዋጥታችሁ ስጡን እያሉ እያንገላቷቸው እንደሚገኙ ተገለፀ።



  በአማራ ክልል በሰሜን ጎንደር ዞን መተማ ወረዳ አብደራፊዕ አካባቢ ተሰማርተው የሚገኙ የገዥው መደብ የፌደራል ፖሊስ አባላት የግል ጥቅማቸውን ለማረጋገጥ ላይና ታች እያሉ እንደሚገኙ የገለፀው ይህ መረጃ እነዚህ ፖሊሶች ገንዘብ ለመሰብሰብ እየተጠቀሙበት ያለው አንዱ መላ በሃብታም ስራ ላይ ተቀጥረው ለሚሰሩ የቀን ሰራተኞች እዚህ ቦታ በሰላም ለመስራት ከፈለጋችሁ ገንዘብ አዋጣችሁ ስጡን አለበለዚያ ግን በዚህ አካባቢ መስራት አትችሉም እያሉ በማስፈራራት ላይ እንደሚገኙ መረጃው አስረድቷል።
   መረጃው ጨምሮ- በነዚህ የፌደራል ፖሊሶች እኩይ ተግባር ሰለባ የሆነው የቀን ሰራተኛ አቶ መኮነን የተባለው ግለሰብ ነጋ ጠባ በላያቸው ላይ እየተፈፀመ ላለው አስነዋሪና ስስት የወለደው ተግባር መፍትሄ እንዲደረግለት በማለት በአካባቢው ወደ ሚገኝ ፖሊስ ጣብያ በመሄድ አቤቱታውን በሚያሰማበት ሰዓት የስርዓቱ የፖሊስ አባላት ግን በህብረተሰቡ ‘ላይ እየደረሰ ላለው በደል ሰምተው መፍትሄ ከመስጠት ይልቅ በአንፃሩ ተመልሰው አንተ ልታደናግር ነው እንጂ በፍፁም የፌደራል ፖሊስ እንደዚህ አይነት ትግባር አይፈፅምም በማለት ሰውየውን በማሰር እያሰቃዩት እንደሚገኙ የደረሰን መረጃ አክሎ አስረድቷል።