Thursday, September 18, 2014

ከመከላከያ ሰራዊት ፈርጥጠው የሚከበሉሉ አባላት በመስፋፋቱ ምክንያት ጭንቀት ውስጥ የገቡት የእዝ ሃላፊዎች ስብሰባ ላይ መጠመዳቸው ተገለፀ።



    ከመከላከያ ሰራዊት ስታፍ ሸልኮ የደረሰን መረጃ እንዳመለከተው የገዢው መንግስት ወታደሮች የማህበራዊ ንሮ ችግርና ፍትሃዊነት የጎደለው አሰራርና ሌለወች ምክንያተወች ተስፋ ቆርጠው ክፍላቸውን በመተው እየከዱ የሚሄዱትን የወታደሮች ቁጥር ከቀን ወደቀን እየጨመሩ መሄዳቸውና የስራዊት ቁጥር እየመነመነ በመሄዱ ምክንያት ጭንቀት ውስጥ የገቡት የእዝ አመራሮች ሳሞራ የኑስና ስራጅ ፈጌሳ የተገኙበት አስቸኳይ ስብሰባ ላይ መቀመጣቸውን የደረሰን መረጃ ገለጸ።
    ስብሰባውን እየመሩ ያሉትን ባለስልጣኖች ይዘውት የቀረቡትን አጅንዳ እየኮበለሉ የሚገኙትን የሰራዊቱ ቁጥር እንዲቀንስ ምን ማድረግ ይገባናል የሚል መሆኑንና መሪዎቹ በጀት መጨመር አለበት የሚል ሃሳብ ቢያቀርቡም በስብሰባው ላይ የተገኙት የእዝ አመራሮች ግን በጀት መጨመር ግዚያዊ እንጂ መሰረታዊ መፍትሄ ሊያመጣ አይችልም ዋናው ፀረ ዴሞክራሲያዊ አሰራራችን ማስወገድ ነው በማለት ሃሳባቸውን እንደገለፁ ለማወቅ ተችሏል።
    በተነሳው አጀንዳ ላይ እልባት ላይ መድረስ የተሳናቸው የስብሰባው መሪዎችና ተሰብሳቢዎቹ መፍትሄ ይሆናል ብሎ ያቀረቡትን ሃሳብ በሌሎቹ ተቀባይነት በማጣቱ እስካሁን ስብሰባውን እየቀጠለ መሆኑንን ምንጮቻችን በላኩልን መረጃ መሰረት ለመረዳት ተችለዋል።