Saturday, September 20, 2014

በነቀምት ከተማ መሰረተ ልማት ባለመኖሩ ምክንያት የከተማዋ ነዋሪዎች ኑሮአቸውን እንዳይመሩ ተቸግረው እንዳሉ ምንጮቻችን ከከተማዋ ገለጹ።



በኦሮሚያ ክልል የነቀምት ከተማ ነዋሪዎች በመሰረተ ልማት እጥረት ምክንያት ተቸግረው እዳሉ የገለጸው መረጃው በተለይም በከተማዋ የንጹህ ውሃ አቅርቦት ባለመኖሩ ምክንያት ሽማግሌዎችና ህጻናት የሚገኙባቸው ለተላላፊ በሽታዎች ተጋልጠው እንደሚገኙ ተገልጿል።
    መረጃው አክሎም የግል ባለ-ሃብቶች የሚገኙባቸው የከተማዋ ነዋሪዎች በውሃ እጥረት ምክንያት እለታዊ ሰራቸውን ሊያከናውኑ እንዳልቻሉና ለኪሳራ ተጋልጠው እንዳሉ በመግለፅ። በነሱ ስር ሆነው የሚሰሩ ሰራተኞችንም ለማባረር መገደዳቸውና። በዚህ የተነሳም የቀን ሰራተኞች በስራ እጥረት እየተሰቃዩ እንደሚገኙ መረጃው አስታውቋል።
     አጋጥሞ ያለውን የውሃ እጥረት መፍትሄ እንዲደረግለት በማለት  ወደ ሚመለከታቸው አካላት ሄደው አቤቱታቸውን ያሰሙ ቢሆኑም በሃላፊዎቹ አጥጋቢ ምላሽ እንዳላገኙ የገለጸው መረጃው በተመሳሳይ ለማህበራዊ አግልግሎት የሚውሉ አላቂ ነገሮች ከከተማዋ በመጥፋታቸው ምክንያት ለነዋሪዎቹ ተጨማሪ ችግር ሆኖባቸው እንዳለ መረጃው ጨምሮ አስረድቷል።