Sunday, October 26, 2014

የሰለኽለኻ ከተማ ነዋሪዎች በሃገሪቱ የተመዘገበ የመሰረተ ልማት እድገት እንደሌለ ጥቅምት 4/2007 ዓ.ም በተካሄደ ስብሰባ ላይ መግለፃቸውን ምንጮቻችን ከከተማዋ አስታወቁ፣


   በትግራይ ሰሜናዊ ምዕራብ ዞን የሚገኙ የሰለኽለኻ ከተማ ነዋሪዎች ባሳለፍነው ሳምንት በከተማዋ አስተዳዳሪ ስብሰባ እንደተደረገላቸው የገለፀው ይህ መረጃ። በስብሰባው ላይ ሃገራችን መልካም በሚባል የእድገት ደረጃ እንደምትገኝ በስርዓቱ ካድሬዎች ለቀረበው ሃሳብ። ተሰብሳቢዎቹም የድሃውን ቤት አፍርሳችሁ ጉቦ ለሰጧችሁ ስላደላችኋቸው እድገት ተመዘገበ ማለታችሁ እጅግ በጣም የሚያሳዝን ጉዳይ ነው በማለት የቀረበውን ሃሳብ እንደተቃወሙት ለማወቅ ተችሏል፣
 በአመራሮች የቀረበውን ሃሳብ ከተቃወሙት ወገኖቻችን መካከል ሓለቃ ተስፋይ አብረሃለይ። ተክለና ሌሎችም ለጊዜው ስማቸው በውል ያልታወቁ የሚገኙባቸው ሲሆኑ። እነዚህ ሰዎች በንግግራቸው በከተማዋ ከ35 በላይ የሚሆኑ ዜጎች ያለምንም ካሳና ተለዋጭ መሬት መኖሪያ ቤታቸው ፈርሶ መጠለያ አጥተው በከባድ ችግር ላይ ወድቀው እያሉ። የልማት እድገት በሃገራችን ታይቷል ማለት የህልም እንጀራ መብላት ማለት ነው ሲሉ፤ የተሰማቸውን ምሬት እንደተናገሩ ያገኘነው መረጃ አክሎ አስረድቷል፣