በትግራይ ምዕራባዊ ዞን
በሰቲት ሁመራ ከተማ መሬት የሌላቸው ወገኖች በመነሃርያው አካባቢ ኮንቴነር ተከራይተው በተለያዩ ስራዎች ተሰማርተው ሲሰሩ የነበሩ
ከ30 በላይ የሚሆኑ ዜጎች በአሁኑ ሰዓት ከ5 አመት በላይ ኮንቴነር ተከራይታችሁ መቆየት አንፈቅድላችሁም ተብለው በአስተዳዳሪዎች
ተገደው እንዲወጡ መደረጋቸውን ምንጮቻችን አስታወቁ፣
በዚህ ምክንያት በችግር ላይ ወድቀው ከሚገኙ ወገኖቻችን መካከል የተወሰኑትን
ለመጥቀስ አቶ አባይ ሓጎስ የሸቀጣሸቀጥና ኮስሞቲክስ ባለቤት፤ ወይዘሮ የሺና ሰላም ደግሞ በሻይ ቤት የሚተዳደሩ እንስቶች መሆናቸውን
የገለጸው መረጃው እነዚህ የችግሩ ሰለባ የሆኑ ዜጎች ኮንቴነር እንዲፈቀድላቸው ወይንም መሬት እንዲሰጣቸው ለአስተዳድሩ አቤቱታቸውን
የቀረቡ ቢሆንም የሚሰማቸው አካል እንዳላገኙ ለማወቅ ተችሏል፣
በዝቅተኛ የኑሮ ሁኔታ ላይ ለሚገኘው የሁመራ ከተማ ነዋሪ ህዝብ የመኖሪያ
መሬት ፍትሓዊ በሆነ መንገድ እየታደለ ባለመሆኑ የተንሳ፤ በከባድ ችግር ላይ ወድቆ እንደሚገኝ በተለያየ ጊዜ በዜናዎቻችን እየገለፅን
መቆየታችን ይታወሳል፣